ሰበታ ከተማ ቅሬታ አቀረበባቸው የተባሉ ረዳት ዳኞች ታገዱ

ሰበታ ከተማ በባህር ዳር ከተማ 4ለ1 በተረታበት ጨዋታ ውጤት ለዋጭ ስህተት ሰርተዋል የተባሉት ፌዴራል ረዳት ዳኛ አሸብር ታፈሰና ፌዴራል ረዳት ዳኛ ባደታ ገብሬ ከዳኝነት መታገዳቸው ታውቋል።

ፌዴራል ረዳት ዳኛ ባደታ ትክክኛ የሆነውን የፍጹም ገ/ማርያም ኳስን በመከልከሉ ፌዴራል ረዳት ዳኛ አሸብር ደግሞ ባህርዳር ያስቆጠራቸውን ትክክል ያልሆኑ ኳሶችን በማጽደቁ ውጤት ለውጠዋል በሚል በዳኞች ኮሚቴ ውሳኔ መሠረት ከነገው የ9ኛ ሳምንት ጨዋታ ውጪ ሆነው ካሉበት ሆቴል እንዲወጡ መወሰኑ ታውቋል።

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport