” ከዋሊያዎቹ ጋር ያደረግነው የሜዳችን ጨዋታ ማሸነፍ አይገባንም ነበር ” ሀሚዱ ጂብሪላ የኒጀር እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት

 

በእልህ እና በቁጭት የዛሬውን ጨዋታ ከድንቅ እንቅስቃሴ ጋር ማሸነፍ የቻሉት ዋልያዎቹ በከፍተኛ ደስታ ላይ ይገኛሉ ።

ከቀናት በፊት ኒጀር ላይ በሚያስቆጭ ሁኔታ ሽንፈትን ካስተናገዱ በኋላ የኒጀር እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለዋልያዎቹ አባለት መሸነፍ እንደማይገባን እና በመልሱ ጨዋታ ይህን ውጤት እንደሚቀለቡሱት መናገራቸውን ለማወቅ ችለናል ።

የኒጀር እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሀሚዱ ጂብሪላ አያይዘውም በጨዋታው ተበልጠው እንደነበር አምነው ለብሔራዊ ቡድናችን በኒጀርም በዛሬው ዕለትም ከፍተኛ የሞራል ድጋፍ ማድረጋቸው ታውቋል ።

© photo – Afroto

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor