የዋልያዎቹ ተጋጣሚ ኒጀር የወዳጅነት ጨዋታ አካሄደ !

 

ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ከ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ጨዋታውን የሚያደርገው የኒጀር ብሔራዊ ቡድን ከ ማሊ አቻቸው ጋር ተገናኝተው አንድ አቻ ሊለያዩ ችለዋል ።

የሀገሪቱ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውስን ደጋፊዎች ተገቢውን የኮሮና ቫይረስ ፕሮቶኮል ጠብቀው ወደ ሜዳ እንዲገቡ በመፍቀድ በውስን ደጋፊዎች በተደረገው ጨዋታ የመሐል ሜዳ ተጫዋቹ ዳሬንኩም ግብ መሪ ቢያደርጋቸውም ማሊዎች እረፍት ከመውጣታቸው በፊት ባስቆጠሩት ግብ አቻ ሊጠናቀቅ ችሏል ።

የኒጀር ብሔራዊ ቡድን በመጪው ስምንት ቀናት ከ ሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን ጋር ሁለቴ እንደሚጫወቱ ተጠቁሟል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor