የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሚጀምርበት ከተማ ታወቀ !
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከ መጋቢት ሰባት 2011 ዓ.ም ጀምሮ ምንም አይነት ውድድሮች ሳይካሄዱ ሲቆዩ የዘንድሮው የውድድር ዓመት የ2013 የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሚጀምርበት ቀን ታህሳስ 3 መሆኑ ሊግ ኮሚቴው ለክለቦች በላከው ደብዳቤ ማሳወቁ ይታወቃል ፡፡
በዚህም መሰረት የ2013 የኢትዮጲያ ፕሪሚየር ሊግ ታህሳስ3/2013 በ6 ስታዲየሞች እንዲጀመር ሲወሰን የመጀመሪያዎቹ 40 ጨዋታዎች ማለትም በአንድ ሳምንት 8 ጨዋታዎች እሚከናወኑ ሲሆን አምስት ሳምንታት አዲስአበባ ላይ እንደሚከናወኑ ሀትሪክ ስፖርት ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል።