በአፄዎቹ ቤት የፊት አጥቂ የነበረው ሙጂብ ቃሲም ከሳምንታት በፊት ከፋሲል ከነማ ጋር በስምምነት በመለያየት ወደ አልጄሪያው ክለብ ጄኤስ ካቢሌ ለመጓዝ አብዛኛውን ነገር ካጠናቀቀ በኋላ ዝውውሩ ከሽፎበት እንደነበር ይታወሳል ።

ከዝወውሩ መክሸፍ ጋር ተያይዞም ከክለቡ ፋሲል ከነማ ጋር ከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ ገብቶ ነበር ። በፋሲል ከነማ ቀሪ የአንድ አመት ኮንትራት ያለው በመሆኑ ወደ ክለቡ እንዲመለስ ቢጠየቅም ሳይመለስ ቀርቶ ስሙ ከሰበታ ከነማ እና ድሬዳዋ ከተማ ጋር በስፋት ሲያያዝ የከረመው ተጫዋቹ ተሰናክሎበት የነበረውን ዝውውር ለማጠናቀቅ በትላንትናው ዕለት ወደ ቱኒዝያ ያቀና ሲሆን ዛሬ ወይም ነገ ወደ አልጀሪያ ተጉዞ ዝውውሩን ያጠናቅቃል ተብሎም ይጠበቃል ።
አስተያየት ይስጡ