ሰበታ ከተማና ድሬዳዋ ከተማ ሙጂብ ቃሲምን ለማስፈረም በየፊናቸው እያደረጉ ያሉት ሙከራዎች ከሽፈዋል።
በተለይ የድሬዳዋ ከተማ አሰልጣኙ ዘማርያም ወ/ጊዮርጊስን ሙጂብና ወኪሉን ይዘው ፌዴሬሽን ቢሄዱም ክለቡ ያስገባው ደብዳቤ እንዳለ ተነግሯቸው ተጨዋቹ ሳይፈርም ቀርቷል። ሰበታ ከተማዎችም ጠንካራ ግንኙነት ፈጥረው ለማስፈረም ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል። ተጨዋቹ እጁ ላይ ውል እያለው ዝውውር የማድረግ መብቱ ሊከለከል አይገባም የሚሉ ወገኖችቢኖሩም ክለቡ የውጪ እድሉ ከተቋረጠ መጫወት ያለበት ለኔ ነው በማለት ጠንካራ አቋሙን በማሳወቁ ጉዳዩ አከራካሪ ሆኗል።
በጉዳዩ ዙሪያ ፕሬዝዳንቱ አቶ ኢሳያስ ጅራ ከፋሲል ከተማ ውጪ ለማንኛውም ክለብ አይፈርምም የሚል ጠንካራ አቋም መያዛቸውን ታማኝ ምነጮቻችን ገልጸዋል።
ሙሉ ለሙሉ ለፋሲል የመጫወት ፍላጎቱ የተሟጠጠበት ሙጂብ ቀጣይ እድል ከፋሲል ከነማና ከፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ መልካም ፍቃድ ላይ የተንጠለጠለ ሆኗል። ክለቡም የተጨዋቹን ግልጋሎት በሙሉ ማግኘት ካልቻለ መጫወት ለማይፈልግለት ተጨዋች ለምን ይህን ያህል እልህ ይጋባል የሚል ቅሬታ የሚያነሱ ወገኖች በርክተዋል።
የተፈጠረውን ሰፊ ልዩነት ለማጥበብ ብቸኛ መፍትሄው ድርድር ብቻ በመሆኑ በቀጣዮቹ ቀናት አዲስ ነገር ሊፈጠር እንደሚችል ይጠበቃል።
አስተያየት ይስጡ