ኤርነስት ሚደንዶርፕ አዲሱን ክለብ ተቀላቅለዋል !

 

ከወራት በፊት ፈረሰኞቹን ለማሰልጠን የተስማሙት ኤርነስት ሚደን ዶርፕ አጥጋቢ ባልሆነ ምክንያት ከጥቂት ሳምንታት ቆይታ በኋላ ከፈረሰኞቹ ጋር ሊለያዩ ችለዋል ።

ኤርነስት ሚደን ዶርፕ ያለ አሰልጣኛን የነበረውን ማሪትዝበርግ ክለብ መቀላቀላቸው ይፋ ሆኗል ።

ኤርነስት ሚደን ዶርፕ ከ ክለቡ ባለቤቶች ጋር ቤተሰባዊ የሆነ ቅርርብ እንዳለቸው ሲገለፅ አዲስ አበባ በነበሩበት ወቅት ስምምንቱን ጨርሰው መሄዳቸው ታውቋል ።

ከደቡብ አፍሪካ በወጣ መረጃ የኤርነስት ሚደን ዶርፕ የቅርብ ሰው የሚባለው የፈረሰኞቹ ጊዜያዊ አሰልጣኝ ዴቪድ ማሂርም በክለቡ ባለቤቶች ጨምሮ በ ሚደን ዶርፕ ጥቆማ በጥብቅ እየተፈለገ እንደሚገኝ ተዘግቧል ።

ፈረሰኞቹ ውሉን ያለከበረውን አሰልጣኝ ኤርነስት ሚደን ዶርፕ የሁለት ወር ደሞዙን በካሳ ክፍያ መቀበላቸው ይታወቃል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor