የመቐለ 70 የሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ሳይሳካ ቀረ

 

የ2 አመት ዕገዳና 5 ሺ ዶላር ይቀጣሉ
ተብሎ ተሰግቷል

የመቐለ 70 እንደርታ ተጨዋቾች በሻምፒየንስ ሊግ ለመሳተፍ የነበራቸው ፍላጎት በካፍ ክልከላ ሳይሳካ ቀረ፡፡
ካፍ ለአንድ ጨዋታ እስከ 16 ተጨዋቾች ቢያዝም የመቐለ 70 እንደርታ ተጨዋቾች ከ11 መብለጥ ባለመቻላቸውና ካፍም ከ16 ውጪ አልቀንስም በማለቱ ዕቅዱ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጅራ ጣልቃ ገብተው የካፍ የውድድር ዳይሬክተርን ቢያናግሩም ከጦርነት ከመጣችው ሊቢያ አንጻር እናንተ እንዴት 3 ተቀያሪ መያዝ አትችሉም በሚል ጥያቄውን ውድቅ ማድረጉ ተሰምቷል፡፡

የሊቢያው ክለብ ካይሮ ባይገባም ለዳኞቹና ኮሚሽነሩ የአየር ቲኬት መላኩ ተነግሯል፡፡ ይህን ተከትሎ መቀለ 70 እንደርታ 5 ሺ ዶላርና የ2 አመት ዕገዳ ሊተላለፍበት እንደሚችልም ተሠግቷል፡፡
11 ተጨዋቾች አዲስ አበባ ቢገኙም ቀሪዎቹ 3 ተጨዋቾች ከመቀለ መምጣት አለመቻላቸው ታውቋል፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport