መቐለ 70 እንደርታ አዳማ ሲሴኮን አስፈረመ

በዘንድሮ የውድድር ዓመት በርከት ያሉ ተከላካዮችን ያሰናበቱት ምዓም አናብስቶቹ የባህርዳሩን ማሊያው ተከላካይ አዳማ ሲሴኮን አስፈርመዋል።

በ2010 በጅማ አባጅፋር ቆይታው የሊጉን ዋንጫ ማንሳቱ የሚታወስ ሲሆን ባሳለፍነው አመት በተሰረዘው የውድድር ዓመት በባህርዳር ከተማ በመጫወት ያሳለፈው አዳማ ሲሴኮ በዘንድሮው አመት ለመቐለ 70 እንደርታ ፊርማውን ማኖሩ ከቀድሞው አሰልጣኙ ገብረመድህን ሀይሌ ጋር ድጋሚ የመገናኘት ዕድል አግኝቷል፡፡