መነሻ ገጽ መቻል ጋናዊው ተከላካይ የቅጣት ገንዘብ ላለመክፈል ከመቻል ጋር ተለያየ
መቻልዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ጋናዊው ተከላካይ የቅጣት ገንዘብ ላለመክፈል ከመቻል ጋር ተለያየ

አጋራ
አጋራ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ቅጣት የተጣለበት ተከላካይ ገንዘብ ላለመመለስ በሚል ከክለቡ ጋር ተለያይቷል።

ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ አምስት አመታት አልፎታል። የሀገሩን ክለብ ሌቨርቲ ፕሮፌሽናልን ለቆ ቅዱስ ጊዮርጊስ በመቀላቀል ከክለቡ ጋር የተሳኩ ጊዜያትን በማሳለፍ የሊጉን ዋንጫ ከፍ አድርጎ ማንሳት የቻለ ሲሆን በ2017 ወደ ሌላኛው የሊጉ ክለብ መቻል በማምራት ክለቡን በሁለት አመት ውል መቀላቀል ችሏል።

የፕሪምየር ሊጉ አክሲዮን ማህበር የፋይናንስ ተቆጣጣሪ ኮሚቴ ያስቀመጥኩትን የገንዘብ አከፋፈል ህግ አልተከተልም በሚል በተለያዩ ክለቦች እና ተጫዋቾች ላይ ቅጣትን ሲያስተላልፍ ጋናዊው የመሐል ተከላካይ ፍሪምፓንግ ሜንሱ ግን አሻፈረኝ በሚል ከሦስት ሚሊዮን ብር በላይ መመለስ ያለበትን ብር ተፈፃሚ አላደርግም በሚል ከጦሩ ጋር በስምምነት ተለያይቶ ወደ ሀገሩ አምርቷል። ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ተጫዋቾች ቅጣታቸውን ተፈፃሚ እያደረጉ ባሉበት በአሁኑ ወቅት ይህ ጋናዊ ተከላካይ ግን ቅጣቱን ተግባራዊ ሳያደርግ ወደ ጋና አምርቶ የቀድሞው ክለቡ አሻንቲ ኮቶኮን ሊቀላቀል እንደሚችልም ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...