የጨዋታ ዘገባ | ወልቂጤ ከተማ ከመመራት ተነስተው ከኢትዮጵያ ቡና ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል

 

በአንደኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ትላንት መጀመሩ የሚታወስ ሲሆን ዛሬ ደግሞ ከረፋዱ አራት ስአት ላይ ኢትዮጵያ ቡናን እና በወልቂጤ ከተማን ያገናኘው ጨዋታ ክትፎዎቹ ከመምራት ተነስተው ነጥብን ተጋርተው 2-2 በሆነ ውጤት ተለያይተዋል።

ሁለቱም ቡድኖች ኳስን ተቆጣጥረው ለመጫወት ሲታትሩ የተስተዋለ ሲሆን በተለይም ከግብ ጠባቂ ጀምረው ወደ ፊት ለማጥቃት የሞከሩት ቡናማዎቹ በመጀመሪያው አጋማሽ ብልጫ ነበራቸው። ከግብ ጠባቂ ኳስ ለመመስረት ፍላጎት የነበራቸው ቡናማዎቹ በተለይ ግብ ጠባቂው አቤል ማሞ ለቡድን አጋሮቹ በማቀበል ላይ ተደጋጋሚ ስህተቶች ተስተውሎበት ተመልክተናል። በዚህም አህመድ ሁሴን አቤል ማሞ ለአበበ ጥላሁን አቀብላለው ሲል በፈጠረው ስህተት አገባው ሲባል ለጥቂት በቋሚው የወጣችበት ወልቂጤ ከተማን መሪ ማድረግ የምትችል ነበረች።

ቡናማዎቹ በበኩላቸው በጥሩ ቅብብል የተገኘችውን ኳስ ፍቅረየሱስ ተክለብርሀን ሲሞክር ጀማል ጣሰው በቀላሉ ተቆጣጥሮበታል። የመጀመሪያውን አጋማሽ ምንም ግብ ሳይስተናገድበት 0-0 በሆነ ውጤተ ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል።

በሁለተኛው አጋማሽ ብልጫቸውን የተጠቀሙት ኢትዮጵያ ቡናዎች ቀዳሚ መሆን ችለዋል። አቡበከር ናስር በራሱ ላይ በተሰራው ጥፋት የተገኘችውን የፍፁም ቅጣት ምት በቀላሉ ማስቆጠር ችሏል። በመልሶ ማጥቃት አቡበከር ናስር እና ታፈሰ ሰለሞን ተቀባብለው ጀማል ጣሰው ያመከናት ኳስ አስቆጪ ነበረች። እንዳለ ደባልቄ የወልቂጤ ከተማዎች የኳስ ቅብብል ስህተት ተጠቅሞ ያገኛትን ኳስ ለአቡበክር ናስር አቀብሎት በሚገባ ተጠቅሞ ለራሱ እና ለቡድኑ ሁለተኛ ግብ ማስቆጠር ችሏል።

ከግቦቹ መቆጠር በኋላ ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ወደ ጨዋታ ቅኝት መግባት የቻሉት ክትፎዎቹ በያሬድ ታደሰ አማካኝነት ግብ አስቆጥረው ልዩነቱን ማጥበብ ችለዋል። የመከላከል ችግር በጉልህ ሲታይባቸው የነበሩት ቡናማዎቹ ግብ ከማስተናገድ አላዳናቸውም። በዚህም የኢትዮጵያ ቡናን ተከላካዮች ስህተት በሚገባ የተጠቀመው ረመዳን ናስር ቡድኑን አቻ የምታደርግ ግብ አስቆጥሮ ነጥብ ተጋርተው እንዲወጡ አስችሏል። ጨዋታው 2-2 አቻ በሆነ ውጤት መጠናቀቅ ችሏል።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor