የጨዋታ ዘገባ | አዳማ ከተማ ጣፋጭ ድል ተቀዳጅቷል !

 

የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሁለተኛ ቀን ዛሬም ቀጥለው ሲካሄዱ ዘጠኝ ጎሎችን ለተመልካች አሳይቶ ተጠናቋል ።

ከምሳ ሰዓት በኋላ በተደረገው መርሐ ግብር በገንዘብ ረገድ በትልቁ ስማቸው ይነሱ የነበሩትን አዳማ ከተማ እና ጅማ አባ ጅፋር ሲያገናኝ አዳማ ከተማዎች ከጨዋታ ብልጫ ጋር አሸንፈው ለመውጣት ችለዋል ።

በርካታ ከዋክብት ተጫዋቾቻቸውን ጨምረው አሰልጣኛቸውን ተነጥቀው የውድድር ዓመቱን የጀመሩት አዳማ ከተማዎች ወደ ግብ በተደጋጋሚ ሲደርሱ የጅማ አባ ጅፋር ግብ አቡበከር ኑሪ በአዳማ ከተማው የኋላሸት ላይ በሰራው ጥፋት ከሜዳ ሲሰናበት የጨዋታውን ሁነት ቀይሮት ተስተውሏል ።

 

ጅማ አባጅፋሮች በዚህ ጨዋታ ላይ ተጠባባቂ ግብ ጠባቂ አለመያዛቸውን ተከትሎ ቀሪዎቹን በርካታ ደቂቃዎች ተከላካያቸውን ኢዳላሚን ናስርን ሲያስገቡ በተለይም በተገቢው ጊዜ ዝውውሮችን አለመፈፀማቸው የነበሯቸውን ግብ ጠባቂዎች እንዳይጠቀሙባቸው አድርጓቸዋል ።

ከዚህ ክስተት በኋላ ይበልጥኑ የተነቃቁት አዳማ ከተማዎች በእለቱ ድንቅ ሆኖ ባመሸው ታፈሰ ሰርካ የፍፁም ቅጣት ምት ግብ ቀዳሚ መሆን ችለዋል ። ከግቡ መቆጠር በኋላ ሁለቱም ቡድኖች ተቀዛቅዘው ሲታዪ አስደንጋጭ የሚባል ሙከራ ሳይሞከር የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ ችሏል ።

በሁለተኛው አጋማሽ አራት ጎሎች ሲስተናገዱበት አዳማ ከተማዎች የጅማ አባ ጅፋርን የመስመር ክፍተቶች በመጠቀም ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ማድረግ ሲችሉ ፍሬ አፍርቶላቸዋል ። ታፈሰ ሰርካ ከመስመር ተሻግሮ የመጣውን ኳስ የአዳማ መሪነት ወደ ሁለት ከፍ ያደረገች ግብ በማስቆጠር የፓውሎስ ጌታቸውን ጅማ አባ ጅፋር አጣብቂኝ ውስጥ ከቷቸው አምሽቷል ።

ከጎሉ መቆጠር በኋላም ተደጋጋሚ ጫናዎችን ሲፈጥሩ የቆዩት አዳማ ከተማዎች የጅማ አባጅፋር ግብ ጣባቂ የተፋውን ኳስ ተቀይሮ የገባው አብዲሳ ጀማል ከመረብ ማሳረፍ ችሏል ። ከዚህ ጎል መቆጠር በኋላ ጅማ አባ ጅፋሮች በተመስገን ደረሰ የማስተዛዘኛ ግብ ሲያስቆጥሩ በጭማሪ ደቂቃ ላይ አብዲሳ ጀማል ለራሱ ሁለተኛውን ለአዳማ ከተማ አራተኛውን ግብ ማስቆጠር ችሏል ።

ውጤቱን ተከትሎ አዳማ ከተማዎች በጊዜያዊነት ሊጉን ሲመሩ ጅማ አባ ጅፋሮች የመጨረሻውን ደረጃ ለመያዝ ተገደዋል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor