የጨዋታ ዘገባ | ሀዋሳ ከተማ የመጀመሪያ ድሉን አሳክቷል

 

በአራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሁለተኛ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡናን ከ ሀዋሳ ከተማ ሲያገናኝ በሀዋሳ ከተማ አሸናፊነት ሊጠናቀቅ ችሏል ።

የመጀመሪያው አጋማሽ በጥቅሉ በ ኢትዮጵያ ቡና የኳስ ቁጥጥር የበላይነት እና አስደንጋጭ ሙከራዎች ሁለቱም ቡድኖች ሳያደርጉበት ሲጠናቀቅ ቡናማዎች እንደ ከዚህ ቀደሙ ኳስን ከኋላ መስርቶ ለመውጣት በሚያደርጉት ጊዜ በመልሶ ማጥቃት ሙከራዎች ሲደረጉባቸው ተስተውሏል ።

ኢትዮጵያ ቡናዎች በመጀመሪያው አጋማሽ የመጀመሪያዎቹ ደቂቃ ላይ አቤል ከበደ ከመስመር ያሻገረውን ኳስ ሀብታሙ ታደሰ ሞክሮት ግብ ጠባቂው ሰሆሆ ሜንሳህ ካዳነበት የሚያስቆጭ ሙከራ ውጪ አስደንጋጭ የሚባልን ሙከራን ሳያደርጉ ለመውጣት ችለዋል ።

ሀዋሳ ከተማዎች በተቃራኒው አልፎ አልፎ በሚያገኙት እድሎች ወደ ግብ ሲቀርቡ ወንድማገኝ የሞከረው እና በቀኝ የግብ አግዳሚ ታካ የወጣችው ኳስ ቀዳሚው ሙከራቸው ነበረች ። ከዚህ ሙከራ በኋላ ወደ ግብ ዳግም መድረስ የቻሉት ሀዋሳ ከተማዎች ዘነበ ከነደ ከመስመር ያሻገረውን ኳስ ብሩክ በየነ በደረቱ አብርዶ ቢሞክረም በቀላሉ ተክለማርያም ሻንቆ ሊቆጣጠረው ችሏል ።

 

የመጀመሪያው አጋማሽ ያን ያህል የግብ እድልን ሳያሳይ ሲጠናቀቅ በሁለተኛው አጋማሽ ጅማሮ ላይ ተመሳሳይ የጨዋታ እንቅስቃሴን ለመመልከት ተችሏል ። ሀዋሳ ከተማዎች በሁለተኛወረ አጋማሽ የማጥቃት አማራጫቸውን ኤፍሬም አሻሞን በማስገባት የማጥቃት ጫናዎችን ለማሳደር ሲሞክሩ ፍሬ አፍርቶላቸው የኢትዮጵያ ቡና ግብ ጠባቂ ተክለማርያም ሻንቆ መሳሳትን ተከትሎ ብሩክ በየነ ሀዋሳ ከተማን ቀዳሚ ማድረግ ችሏል ።

ከግቡ መቆጠር በኋላ ሀዋሳ ከተማዎች በተመሳሳይ የጨዋታ እንቅስቃሴ በረጃጅም ኳስ ለብሩክ በየነ በሚጣሉ ኳሶች የግብ እድሎችን መፍጠር ቢችሉም ከሙከራነት መዝለል አልቻሉም ። ቡናማዎቹ ከመጀመሪያው አጋማሽ ይበልጥኑ በተቀዛቀዙበት የጨዋታ እንቅስቃሴ አብበከር ናስር ከቋሞ ኳስ ተሻግሮለት ከወጣችበት የግብ ሙከራ ውጪ አስደንጋጭ ወይም ለግብ የቀረበ ሙከራን ማድረግ ሳይችሉ ጨዋታው ተጠናቋል ።

ኢትዮጵያ ቡና የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ ሽንፈት ሲያስተናግዱ አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት የመጀመሪያ ድላቸውን ከቡናማዎቹ ላይ ሶስት ነጥብ በመውሰድ ማሳካት ችለዋል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor