By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: የጦና ንቦቹ የሊጉን መሪ ሲረቱ አዞዎቹ አፄዎቹን በድጋሚ አሸንፈዋል
Share
Notification Show More
Latest News
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ
ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች
የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
ፋሲል ከነማወላይታ ድቻዜናዎችአርባምንጭ ከተማየጨዋታ ዘገባኢትዮጵያ መድህን

የጦና ንቦቹ የሊጉን መሪ ሲረቱ አዞዎቹ አፄዎቹን በድጋሚ አሸንፈዋል

Habtamu Mitku
Habtamu Mitku 1 year ago
Share
SHARE

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 20ኛ ሳምንት የሶስተኛ ቀን ጨዋታዎች በዛሬው ዕለት ተደርገዋል።

በዕለቱ ቀዳሚ መርሐግብር የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ መድን በወላይታ ድቻ 1 ለ 0 ተሸንፏል።

በጨዋታው 6ኛ ደቂቃ ላይ ፀጋዬ ብርሀኑ ያስቆጠረው ግብ ወላይታ ድቻን አሸናፊ ለማድረግ በቂ ነበር።

ፀጋዬ ብርሀኑ ግቡን ያስቆጠረው ቴዎድሮስ ታፈሰ ከማዕዘን ያሻገረውን ኳስ በግንባር በመግጨት ነው።

- ማሰታውቂያ -

ከተከታያቸው ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሰባት የማስፋት ዕድል የነበራቸው መድኖች በቀጣዮቹ የጨዋታው ደቂቃዎች ውጤቱን ለመቀየር ያደረጉት ጥረት ውጤታማ አልሆነም።

ወላይታ ድቻ ድሉን ተከትሎ ነጥቡን 27 አድርሶ በጊዜያዊነት 7ኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ሲችል 35 ነጥቦችን የሰበሰበውን መድን ከሀድያ ሆሳዕና በአራት ነጥቦች ርቆ በመሪነቱ ቀጥሏል።

ሁለቱ ቡድኖች ከሰባት ጨዋታዎች በፊት በተመሳሳይ ስታድየም ባደረጉት ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን 2 ለ 1 አሸንፎ እንደነበር አይዘነጋም።

በ21ኛው ሳምንት መርሐግብር ኢትዮጵያ መድን ከድሬዳዋ ከተማ እንዲሁም ወላይታ ድቻ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ይጫወታሉ።

በዕለቱ ሁለተኛ መርሐግብር ከአመሻሽ 12:00 ጀምሮ በተደረገው ጨዋታ አርባምንጭ ከተማ ፋሲል ከነማን በተመሳሳይ 1 ለ 0 ረቷል።

ከቅዱስ ጊዮርጊስ በውሰት ውል አርባምንጭ ከተማን የተቀላቀለው ታምራት ኢያሱ ጨዋታው በጀመረ በ117ኛው ሰከንድ ኳስ እና መረብን አገናኝቷል።

ግቡን ሲያስቆጥር ማልያውን በማውለቁ ምክንያት የማስጠንቀቂያ የቢጫ ካርድ የተመለከተው ታምራት በ15ኛው ደቂቃ ላይ በማርቲን ኪዛ ላይ በሰራው ጥፋት በሁለተኛ የቢጫ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

አፄዎቹ በቀጣዮቹ ደቂቃዎች ላይ በተደጋጋሚ ወደ አርባምንጭ ከተማ የግብ ክልል ለመድረስ ቢጥሩም የአርባምንጭ ከተማ የኋላ መስመር ይህን የፈቀደ አልነበረም።

በተከታታይ ሶስት ጨዋታዎች ከድል ጋር ተራርቀው የነበሩት አርባምንጭ ከተማዎች ዳግም ከድል ጋር የተገናኙበት ጨዋታም ሆኗል።

አዞዎቹ በመጀመሪያው ዙር ጨዋታም አበበ ጥላሁን በ5ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠረው ብቸኛ ግብ በተመሳሳይ 1 ለ 0 ማሸነፋቸው ይታወሳል።

አዞዎቹ ማሸነፋቸውን ተከትሎም ነጥባቸውን 27 በማድረስ የ6ኛን ደረጃን በጊዜያዊነት መቆናጠጥ ችለዋል።

በቀጣይ ሳምንት መርሐግብር ፋሲል ከነማ ከባህርዳር ከተማ እንዲሁም አርባምንጭ ከተማ ከአዳማ ከተማ ይጫወታሉ።

You Might Also Like

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ

አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ

የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Habtamu Mitku
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article አፄዎቹ ግብ ጠባቂ እና አጥቂ አስፈርመዋል
Next Article ባህርዳር ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን በሰፊ ውጤት ሲረታ መቻል እና ድሬዳዋ ከተማ ነጥብ ተጋርተዋል

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
ሪፖርትመቐለ 70 እንደርታሰበታ ከተማ

ሪፖርት | መቐለ 70 እንደርታዎች መሪነታቸውን ያስቀጠሉበትን ድል አስመዘገቡ

ዳዊት ብርሀነ By ዳዊት ብርሀነ 6 years ago
የፋሲል ከተማው የኃላ ደጀን አይናለም ሀይለ በነገው እለት ልምምድ ይጀምራል
በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ተጠባቂውን ጨዋታ ማን በድል ይወጣል?
ወልቂጤ ከተማ አዳነ ግርማን የግሉ አድርጓል
ወልቂጤ ከተማ ያቀረበው አቤቱታ ውድቅ ተደርጓል!!
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?