መነሻ ገጽ ባህርዳር ከተማ ፋሲል ከነማና ባህርዳር ከተማ ነጥብ ተጋሩ!
ባህርዳር ከተማዜናዎችየጨዋታ ዘገባፋሲል ከነማ

ፋሲል ከነማና ባህርዳር ከተማ ነጥብ ተጋሩ!

አጋራ
አጋራ

በአቤኔዘር አበበ

በአማራ ደርቢ ፋሲል ከነማና ባህርዳር ከተማ ነጥብ ተጋሩ!

በሁለቱ የአማራ ክለቦች መካከል በተደረገው ተጠባቂ ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ ጥሩ የጨዋታ ፍሰትና የማጥቃት እንቅስቃሴ ታይቷል። ፋሲል ከነማ በተሻለ የማጥቃት እንቅስቃሴ ግብ ማስቆጠር ችሏል።ናትናኤል ገብረጊዮርጊስ በሚያምር ሁኔታ አመቻችቶ ያቀበለውን ኳስ ጄሮም ፊሊፕ ወደ ግብነት በመቀየር ፋሲል ከነማን መሪ አድርጎታል። በዚህም የመጀመሪያው አጋማሽ ፋሲል ከነማ 1-0 በሆነ ውጤት መምራት ችሏል።በሁለተኛው አጋማሽ ጨዋታው በተሻለ ፉክክር የቀጠለ ሲሆን፣ ፋሲል ከነማ በ78ኛው ደቂቃ የመሪነቱን ልዩነት አስፍቷል። ዳግም አወቀ አመቻችቶ ያቀበለውን ኳስ ታምራት እያሱ ወደ ግብነት በመቀየር ለፋሲል ከነማ ሁለተኛውን ግብ አስቆጥሯል።ባህርዳር ከተማ ግን በቀላሉ እጅ የሰጠ ሲሆን፣ ከደቂቃ ወደ ደቂቃ የጨዋታ አቅሙን እያሻሻለ በመምጣት በ83ኛው ደቂቃ ወደ ጨዋታው ተመልሷል። መሳይ አገኝው አመቻችቶ ያቀበለውን ኳስ አንተነህ ተፈራ በመረብ ላይ በማሳረፍ የቡድኑን የመጀመሪያ ግብ አስቆጥሯል።በመጨረሻዎቹ የጨዋታ ደቂቃዎች ግፊቱን ያሳደገው ባህርዳር ከተማ በጭማሪ ደቂቃ 90+2 አንተነህ ተፈራ በድጋሚ ግብ በማስቆጠር የግል ሁለተኛ ግቡንና ለቡድኑ የእኩልነት ግብ አስቆጥሯል።በዚህም ባህርዳር ከተማ ከ2-0 መመራት ተነስቶ ጨዋታውን 2-2 በሆነ ውጤት በማጠናቀቅ አንድ ነጥብ ወደ ነጥብ ሰንጠረዡ ማከል ችሏል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...