መነሻ ገጽ ዜናዎች ነገሌ አርሲና ሀላባ ከተማ ድል ቀናቸው!
ዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

ነገሌ አርሲና ሀላባ ከተማ ድል ቀናቸው!

አጋራ
አጋራ

በአቤኔዘር አበበ

በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአምስተኛ ሳምንት ጨዋታ ነገሌ አርሲ ሸገር ከተማን 2-1 በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥቦችን ሲያገኝ፣ በሌላኛው ጨዋታ ሀላባ ከተማ ሀድያ ሆሳዕናን 2-1 በመርታት ወደ ድል ተመልሷል።

በአምስተኛው ሳምንት ጨዋታ ነገሌ አርሲ ከሸገር ከተማ ጋር ባደረገው ፍልሚያ በመጀመሪያው አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች ጥሩ እንቅስቃሴ በማሳየት ወደ ተጋጣሚያቸው የግብ ክልል በተደጋጋሚ ደርሰዋል። ይሁንና የተሻለ ዕድል የፈጠረው ነገሌ አርሲ በ40ኛው ደቂቃ ከቤ ቡዙኔ በጥሩ ሁኔታ ያቀበለውን ኳስ ሃቢብ ከማል ወደ ግብነት በመቀየር ቡድኑን መሪ አድርጓል። አጋማሹም በነገሌ አርሲ 1-0 መሪነት ተጠናቋል።

ከዕረፍት መልስ ሁለቱም አሰልጣኞች የተጫዋች ቅያሪ በማድረግ ጨዋታውን ለመቀየር ጥረት አድርገዋል። በ65ኛው ደቂቃ ኮሊን ኮፊ በአስደናቂ አጨራረስ ለነገሌ አርሲ ሁለተኛ ጎል አስቆጥሯል። ሸገር ከተማም የተጋጣሚውን ተከላካዮች መዘናጋት ተጠቅሞ ወጣቱ አጥቂ ዳዊት ካሳው አንድ ጎል ቢያስቆጥርም ጨዋታውን ከሽንፈት መታደግ አልቻለም። በመጨረሻም ነገሌ አርሲ 2-1 አሸንፏል።

በሌላ በለላኛ ጨዋታ ሀላባ ከተማ ሀድያ ሆሳዕናን 2-1 አሸንፏል። በጨዋታው ሀላባ ከተማ ከጅምሩ የተሻለ የጨዋታ ብልጫ ወስዶ ተንቀሳቅሷል። ናትናኤል ሰለሞን በጠባብ አንግል በመምታት ኳሷን መረብ ላይ በማሳረፍ ሀላባ ከተማን መሪ አድርጓል። የመጀመሪያው አጋማሽም በሀላባ ከተማ 1-0 መሪነት ተጠናቋል።

ከዕረፍት መልስ ጨዋታው እንደተጀመረ በ46ኛው ደቂቃ ሽመከት ጉግሳ በጥሩ ሁኔታ ያመቻቸውን ኳስ ፍሬው ሰለሞን ወደ ግብነት በመቀየር የሀላባ ከተማን መሪነት ወደ 2-0 አሳድጓል። ሀድያ ሆሳዕና በ56ኛው ደቂቃ ያገኘውን የፍጹም ቅጣት ምት ደስታ ዋሚሾ ወደ ግብነት በመቀየር የግብ ልዩነቱን ቢያጠብም ከዚያ በላይ ጎል ማስቆጠር አልቻለም። በመጨረሻም ሀላባ ከተማ 2-1 በሆነ ውጤት ድል አድርጓል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...