የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
1. ራያን ኦቢን (ሀላባ ከተማ) : ክለቡ ከ ወላይታ ድቻ ጋር ባደረገው የ 4 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ79ኛ ደቂቃ ላይ ከግብ ክልል ውጭ ኳስ በእጅ በመያዝ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ።
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 63 በተቁ1 (ሀ) እና በተቁ 2 መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር3000 /ሶስት ሺህ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
2. ኢትዮ ኤሌትሪክ ክለቡ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ4 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የኢትዮ ኤሌትሪክ ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- ሙከረም ረሺድ
- አቤል ሀብታሙ
- አሸናፊ ጥሩነህ
- ኦሊዮንዚ ናፊያን
- ካሌብ ስቲፍ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 / አምስት ሺ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
3. ፋሲል ከነማ ክለቡ ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር ባደረገው የ4 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የፋሲል ከነማ ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- ፍሬዘር ካሳ
- ሮማሪክ ዲንሆ
- ምኞት ደበበ
- ዳግም አወቀ
- ኪሩቤል ዳኜ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/
እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
4. ኢትዮጵያ ቡና : ክለቡ ከ ኢትዮ ኤሌትሪክ ጋር ባደረገው የ4ኛ ሳምንት የእግር ኳስ ጨዋታ፣ የክለቡ ደጋፊዎች 5 ወንበሮችን ስለመንቀላቸው እና 2 ወንበሮችን ስለመሰበራቸው ሪፖርት ቀርቦበታል። ስለሆነም ክለቡ በአጠቃላይ የተነቀሉትንና የተሰበሩትን 7 ወንበሮች እንዲያሠራ ወይም የስታዲየሙ ባለቤት አሠርቶ የሚያቀርበውን ወጪ እንዲከፍል ወስኗል።
አስተያየት ይስጡ