መነሻ ገጽ ሀዋሳ ከተማ የሊጉ መሪ ሲዳማ በድል ሲጓዝ ኢትዮጵያ ቡና እና ኤሌክትሪክም አሸንፈዋል
ሀዋሳ ከተማሲዳማ ቡናባህርዳር ከተማአርባምንጭ ከተማኢትዮ-ኤሌክትሪክኢትዮጵያ ቡናወላይታ ድቻዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባፋሲል ከነማ

የሊጉ መሪ ሲዳማ በድል ሲጓዝ ኢትዮጵያ ቡና እና ኤሌክትሪክም አሸንፈዋል

አጋራ
አጋራ

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ሲያሰፋ ኢትዮጵያ ቡና እና ኤሌክትሪክ በበኩላቸው ወሳኝ ውጤትን አስመዝግበዋል።

አዳማ ላይ የሊጉን መሪነት ሲዳማ ቡናን ብዙም ከላይ ካሉት ያልራቀውን ፋሲል ከነማን ያገናኘው ጨዋታው ሲዳማ ቡናዎች ጣፋጭ ድል አሳክተውበታል። በሁለቱም ቡድኖች በኩል በመጀመሪያውም ይሁን በሁለተኛው አጋማሽ ተመሳሳይ አቀራረብን ያስተዋልን ሲሆን ጨዋታው ያለ ጎል ይጠናቀቃል ተብሎ ሲጠበቅ በጭማሪው 90+2 ደቂቃ ላይ መስፍን ታፈሠ ከግራ መስመር ታግሎ ያሻማውን የፋሲሉ ተከላካይ ዋሳዋ ጂኦፎሪ ከብለስ ናጎ ጋር ለማውጣት ጥረት ሲያደርግ በራሱ መረብ ላይ ያሳረፋት ኳስ ጨዋታው በመጨረሻም በሲዳማ ቡና 1ለ0 ሊጠናቀቅ ችሏል።

ከሊጉ መሪ ቀጥሎ በደረጃ ሰንጠረዡ የተቀመጠው ሀዋሳ ከተማ ከወላይታ ድቻ ጋር 1ለ1 በማጠናቀቁ ነጥብ ተጋርቶ ለመውጣት ተገዷል። በኳስ ቁጥጥሩም ይሁን በብዙ ረገድ ሀዋሳ ከተማዎች የተሻሉ ቢመስልም ጎልን ቀድመው ያስቆጠሩት ግን የጦና ንቦቹ ናቸው። 34ኛው ደቂቃ ከአጥቂው ቴዎድሮስ ሀይለማርያም ያቀበለውን ሌላኛው ቴዎድሮስ ታፈሠ መረብ ላይ አሳርፎታል። ጨዋታው ሊጠናቀቅ በተሰጠው ጭማሪ 45+1 ደቂቃ ሽመልስ በቀለ የግል ጥረቱን ተጠቅሞ የሰጠውን ወጣቱ ብሩክ ታደለ ሀዋሳን አቻ ማድረግ ችሏል።

ከዕረፍት መልስ ሐይቆቹ አሸንፈው ለመውጣት ሜዳ ላይ የተሻለውን ብልጫ በመውሰድ ቢንቀሳቀሱም ጨዋታው ተጨማሪ ጎል ሳይታይበት 1ለ1 ተፈፅሟል።

ሀዋሳ ላይ ኢትዮጵያ ቡና 2ለ0 በሆነ ውጤት ባህርዳር ከተማን ረቷል። ጨዋታውን በጥሩ ተነሳሽነት የጀመሩት ቡናማዎች 15ኛው ደቂቃ አወዛጋቢ በሆነ መልኩ ከግራ የተሰጠውን የቅጣት ምት በፍቃዱ አለማየሁ ሲያሻማ የባህርዳር ተከላካዮች በግንባር ገጫጭተው የደረሰውን ኳስ አዲሱ ፈራሚ ቢኒያም ጌታቸው በመጀመሪያ ቋሚነቱ በግንባር ጎል አስቆጥሯል። ከዚህች ጎል በኋላ ባህርዳሮች የፍፁም ቅጣት ምት ቢያገኙም ግርማ ዲሳሳ መቶ የግብ ዘቡ ዳላንድ ኢብራሂም ከመለሳት አጋጣሚም በኋላ ሌላ ዕድል አምክነዋል።

ከዕረፍት መልስ በብዙ መልኩ ተሻሽለው የቀረቡ የሚመስሉት ባህርዳሮች ቢሆኑም 56ኛው ደቂቃ ከዲቫይን ዋቹኩዋ ዘላለም አባተ የደረሰውን ኳስ ኢትዮጵያ ቡና 2ለ0 ማሸነፍ እንዲችል ያደረገች ጎልን አስቆጥሯል።

ማምሻውን አርባምንጭ ከተማን ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ያገናኘው መርሀግብር በአምስት ጎሎች የተንበሸበሸ ነበር። ፓትሪክ ሲቦማኔ ከአርባምንጭ ተከላካዮች ዝንጉነት ያገኛትን ኳስ በግሩም ሁኔታ ከመረብ አሳርፎ ኤሌትሪክን መሪ ሲያደርግ 16ኛው ደቂቃ ላይ ቶጓዊው የአርባምንጭ ግብ ጠባቂ እድሪሱ ኦጎዶጆ በተሳሳተ መልኩ ያቀበለውን ኳስ ፈጥኖ ያገኘው አቤል ሀብታሙ ሌላ ተጨማሪ ግብ ሲያክል 43ኛው ደቂቃ ላይ በጨዋታው ጥሩ ጊዜ ከነበረው ፓትሪክ ሲቦማኔ የደረሰውን አማካዩ አንዋር በድሩ ሦስተኛ ጎል ማድረግ ችሏል።

ከዕረፍት መልስ ከዕረፍት መልስም ከቆሙበት የቀጠሉት ኤሌክትሪኮች 48ኛው ደቂቃ የሀሰን ሁሴን ጥሩ የማቀበል ዕይታ ታክሎበት አቤል ሀብታሙ ለራሱ ሁለተኛ ለክለቡ አራተኛ ጎሉን ሲያስቆጥር የመጨረሻዎቹን ደቂቃዎች በተሻለ የተነቃቁት አዞዎቹ ተቀይሮ በገባው ይገዙ ቦጋለ አማካኝነት ከሽንፈት ያላዳነቻቸውን ጎል ቢያገኙም ጨዋታው በኢትዮ ኤሌክትሪክ 4ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

አንጋፋው አሰልጣኝ በስማቸው የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ሊገነባላቸው ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻውን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት...