ፈረሰኞቹ ከሁለተኛ ተጫዋቻቸው ጋር መለያየታቸው ታውቋል።
በአማካይ ስፍራ ላይ ከተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ጀምሮ በቅዱስ ጊዮርጊስ መለያ ሲጫወት የነበረው የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ አፈወርቅ ሐይሉ ከክለቡ ጋር በስምምነት መለያየቱን ያገኘሁት መረጃ ይጠቁማል።
የቀድሞው የወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ እና ባህርዳር ከተማ አማካይ ከአቤል ያለው በመቀጠል ክለቡን የለቀቀ ተጫዋች ሲሆን ቀጣዩ ማረፊያው ለማድረግም ከሦስት የሊጉ ክለቦች ጋር ንግግር ላይ መሆኑን ጭምር ስምቻለሁ።

አስተያየት ይስጡ