የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ዕግዱን ተፈፃሚ ማድረግ ካልቻለ ለየትኛውም ክለብ መፈረም አይችልም ለምን ?
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ ከታዩ ድንቅ አማካዮች መካከል አንዱ ሱራፌል ዳኛቸው ነው። ከመተሐራዋ መርቲ የተነሳው የእግር ኳስ ህይወቱ በአዳማ ከተማ ወጣት እና ዋናው ቡድን ወደ ፋሲል ከነማ በማምራትም የማይረሱ አምስት የውድድር አመታቶችን በክለቡ ተጫውቶ አሳልፏል። በአፄዎቹ ቤት ከነበረው ባሻገር በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ባሳየው አቋም ወደ አሜሪካ ተጉዞ ለዲሲ ዩናይትድ ቢፈርምም በክለቡ የአንድ አመት ከዘጠኝ ወራት ጊዜን ብቻ በማሳለፍ ከወራቶች በፊት ወደ ሀገር ውስጥ መምጣቱ ይታወሳል።
ተጫዋቹ በግል ከገጠመው አንዳንድ ጉዳይ የተነሳ በዕረፍት ላይ የነበረ ሲሆን በቅርቡ ወደ ፋሲል ከነማ ለማምራት ሙሉ በሙሉ ከተስማማ በኋላ በመጨረሻም ከሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ጋር ድርድር በማድረግ ሂደት ላይ ይገኛል። አሁን በደረሰኝ መረጃ መሠረት ሱራፌል ለአሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና የቀድሞው የፋሲል ቡድን መሪ ሀብታሙ ዘዋለ በኩል በብድር መልክ ዋስ ሆነውት ከፋሲል ከነማ የተቀበለውን ከግማሽ ሚሊዮን ብር መመለስ ባለመቻሉ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን ተጫዋቹን እስከ አሁን አግዶት ይገኛል።
ገንዘቡን በመክፈል ይህን ዕግድ ማስነሳት እስካልቻለ ድረስ ተጫዋቹ ወደየትኛውም ክለብ ማምራት እንደማይችል አረጋግጫለሁ።
አስተያየት ይስጡ