By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: የጦና ንቦቹ እና ቡናማዎቹ ወሳኝ ድል አሳክተዋል
Share
Notification Show More
Latest News
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ
ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች
አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
ሸገር ከተማነጌሌ አርሲየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግኢትዮጵያ ቡናወላይታ ድቻዜናዎችድሬዳዋ ከተማአዳማ ከተማመቐለ 70 እንደርታየጨዋታ ዘገባመቻል

የጦና ንቦቹ እና ቡናማዎቹ ወሳኝ ድል አሳክተዋል

ቴዎድሮስ ታከለ
ቴዎድሮስ ታከለ 1 week ago
Share
SHARE

በሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ በጎል የጎመራው የሸገር እና አዳማ ጨዋታ 3ለ3 በሆነ የአቻ ውጤት ሲቋጭ መቻል ከ መቐለ ያለ ጎል ድቻ እና ቡናማዎቹ በድል ቋጭተዋል።

ሸገር ከተማ 3-3 አዳማ ከተማ

ሀዋሳ ላይ ሁለቱን የኦሮሚያ ክለቦች ያገናኘው ጨዋታ በሚገርም የሜዳ ላይ ፉክክር ታጅቦ በመጨረሻም በአቻ ውጤት መጠናቀቅ ችሏል። በመጀመሪያዎቹ አስር ደቂቃዎች ጥሩ ለመንቀሳቀስ የቻሉት አዳማዎች 10ኛው ደቂቃ በጥሩ ቅብብል ከቀኝ አቡበከር ሳኒ የሰጠውን ኳስ ተጠቅሞ አህመድ ሁሴን ከመረብ በማሳረፍ አዳማን መሪ ማድረግ ችሏል። ከዕረፍት መልስ በይበልጥ ተሻሽለው የቀረቡት ሸገሮች 60ኛው ደቂቃ ናትናኤል ዘለቀ ከብዙአየው ሰይፈ የነጠቀውን ኳስ ከፍ አድርጎ የሰጠውን ኳስ ቢኒያም ፍቅሬ በጥሩ አጨራረስ ከመረብ በማሳረፍ ቡድኑን አቻ ማድረግ ችሏል።

በቀጣዮቹም ደቂቃዎች በርካታ የግብ ዕድሎችን በመፍጠሩ የተዋጣላቸው ሸገሮች እጅግ የሚያስቆጩ ዕድሎችን ቢያገኙም በቀላሉ ሲያመክኑ ተስተውሏል። 87ኛው ደቂቃ ጀቤሳ ሜኤሳ ከተከላካይ ጀርባ የተጣለለትን ኳስ በድንቅ አጨራረስ ከተመሪነት ወደ መሪነት ክለቡን ማሸጋገር ችሏል። አዳማ ከተማዎች መንቃቅን በጀመሩበት የመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች 90+1 ላይ ከጉዳት የተመለሰው አላዛር ሽመልስ ከሳሙኤል ዮሐንስ የተሻገረውን ኳስ በግንባር ገጭቶ አዳማን ወደ ጨዋታ የመለሰ ሲሆን አሁንም አላዛር እጅግ አስደናቂ ሌላ ጎል በማከል አዳማን ወደ መሪነት ማሸጋገር ችሏል።

- ማሰታውቂያ -

ጨዋታው ሊጠናቀቅ በቀሩት ሽርፍራፊ ሰከንዶች ውስጥ ለአዳማ ሁለት ጎል ያስቆጠረው አላዛር ሽመልስ በራሱ የጎል ክልል ኳስን በእጅ በመንካቱ የተሰጠውን የፍፁም ቅጣት ምት ሔኖክ አዱኛ ከመረብ አሳርፎት በመጨረሻም ጨዋታው 3ለ3 ሊጠናቀቅ ግድ ብሏል።

ነገሌ አርሲ 0-1 ኢትዮጵያ ቡና

እጅግ ጠንካራ ፉክክርን ያስተዋልንበት የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የምሽቱ መርሀግብር በበርካታ ደጋፊዎች የታጀበ ነበር። ነገሌዎች በተሻለ መንቀሳቀስ የቻሉበት የመጀመሪያው አጋማሽ በመከራ ረገድ ግን ቡናማዎቹ ሻል ያሉበት እንደነበር ተስተውሏል። ከዕረፍት መልስ ነገሌዎች ጥሩ አጀማመር ለማድረግ ጥረቶች ያልተለያቸው ቢሆንም የኋላ ኋላ ግን ኢትዮጵያ ቡናዎች በሽግግር የዋዛ አልነበሩም።

በዚህም የተነሳ 87ኛው ደቂቃ ተቀይሮ የገባው ኤርሚያስ ሹምበዛ ወደ ሳጥን ከግራ ሲያሻማ ቦና ቦካ በእጅ ኳስን በመንካቱ የተሰጠውን የፍፁም ቅጣት ምት የቡናማዎቹ አምበል ራምኬል ጀምስ ከመረብ አዋህዶ ቡድኑን አሸናፊ አድርጓል።

ድሬዳዋ ከተማ 0-2 ወላይታ ድቻ

ወላይታ ድቻ ተከታታይ ሁለተኛ ድሉን አሳክቷል። ተመጣጣኝ የሚመስል መልክ ከነበረው የመጀመሪያው አጋማሽ በሁለተኛው በአንፃራዊነት ድቻዎች የተሻሉ ነበሩ ለዚህም መነሻው 49ኛው ደቂቃ ላይ የድሬዳዋው ድልአዲስ ገብሬ መሳይ ኒኮል ላይ በሰራው አደገኛ ጥፋት በቀይ ካርድ መውጣቱ ቡድኑ የጎዳው መስሏል።

65ኛው ደቂቃ የቁጥር ብልጫን የያዙት የጦና ንቦቹ ካርሎስ ዳምጠው ከሳጥን ውጪ አስደናቂ ጎል በማስቆጠር ቡድኑ መሪ አድርጓል። 83ኛው ደቂቃ ያሬድ ዳርዛ ከግራ ወደ ውስጥ አሻምቶ ዮናታን ኤልያስ የተከላካዮች ስህተት ታክሎ ካርሎስ ዳምጠው ጋር የደረሰችውን ኳስ ለራሱም ለቡድኑም ሁለተኛ ጎል በማድረግ ጨዋታው 2ለ0 መጠናቀቅ ችሏል።

መቻል 0-0 መቐለ 70 እንደርታ

በመጀመሪያው አጋማሽ ተመጣጣኝ በሁለተኛው አጋማሽ ደግሞ መቻሎች የተሻለውን ቆይታ ያሳዩበት የአዳማው የምሽት ጨዋታ ያለ ጎል ተቋጭቷል።

You Might Also Like

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ

አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ

የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
Previous Article ኢትዮጵያዊቷ አትሌት በዶፒንግ ምርመራ በቋንቋ ችግር ለሁለት ዓመታት እገዳ ተጣለባት!
Next Article ኢትዮጵያ ቡና አማካይ አስፈረመ
Leave a comment

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
ዜናዎችኢትዮጵያን በውጪ

የዋልያዋቹ ኮከብ ወደ ሜዳ ተመልሷል !

kidus Yoftahe By kidus Yoftahe 6 years ago
ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ | አዳማ ከተማ ከጅማ አባጅፋር
ሀትሪክ ጋዜጣዎ ነገ (ረቡዕ) በልዩ ዝግጅት ተወዳጅዋና የመጀመሪያዋ ባለ ቀለም ጋዜጣዎ ሀትሪክ ነገ (ረቡዕ) በእጅዎ ትገባለች
የጨዋታ ዘገባ | በሊጉ መሪዎች መካከል የተደረገው ጨዋታ ግብ ሳያስተናግድ ተጠናቋል
18ቱ ዳኞች ኮቪድ 19 የለባችሁም ተባሉ
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?