By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: ሪፖርት | ንግድ ባንክ እና መቻል ባለ ድል ሆነዋል
Share
Notification Show More
Latest News
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ
ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች
አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግወልዋሎዜናዎችድሬዳዋ ከተማኢትዮጵያ ንግድ ባንክየጨዋታ ዘገባመቻል

ሪፖርት | ንግድ ባንክ እና መቻል ባለ ድል ሆነዋል

hatricksport team
hatricksport team 4 months ago
Share
SHARE

በሀዋሳ ዩኒቨርሰቲ ስታዲየም በተደረጉ የሳምንቱ መባቻ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና መቻል በድል አጠናቀውበታል።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2-0 ድሬዳዋ ከተማ

ተመጣጣኝ አጀማመር በነበረው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ፈጣን አጀማመርን ያደረጉት ንግድ ባንኮች በመጀመሪያው አጋማሽ አዲስ ግደይ በጥሩ ዕይታ ሰጥቶት ብሩክ ብፁአምላክ ቋሚ ብረቱ በመለሰበት አጋጣሚ አስደንጋጭ ሙከራን በማድረጉ ቀዳሚ ነበሩ።። በእንቅስቃሴ በተወሰነ ረገድ ይበለጡ እንጂ በጥልቅ አጨዋወት ሙከራን ከማድረግ ያልቦዘኑት ድሬዎች መስዑድ ከቅጣት አሻምቶ ተጨራርፋ የግብ ዘቡ ፓላክ ቾል ያወጣት እና አብዱሰላም የሱፍ ነፃ አጋጣሚን አግኝቶ ሳይጠቀም የቀረበት ተጠቃሾቹ ሙከራዎች ሆነዋል።

ተጋጣሚያቸው ሲያጠቃ መከላከሉን በአግባቡ መቆጣጠር ላይ ውስንነቶች የነበሩባቸው ድሬዎች 42ኛው ደቂቃ በፈጣን መልሶ ማጥቃት ሳይመን ፒተር ጎል አስቆጥሮ ሀምራዊ ለባሾቹን ቀዳሚ ማድረግ ችሏል። ጎልን ካስቆጠሩ በኋላ ይበልጥ መነቃቃት የቻሉት ንግድ ባንኮች ተጨማሪ የግብ ዕድልን ቢያገኙም ወደ ጎልነት መለወጥ ሳይችሉ አጋማሹ ተገባዷል።

- ማሰታውቂያ -

ከዕረፍት መልስ ጨዋታው ሲመለስ ይበልጥ የድሬዳዋ ከተማ ሦስተኛው የሜዳ ክፍል ላይ ደጋግመው የሚገኙት ንግድ ባንኮች በርካታ የጎል ዕድሎችን አግኝቶ የተከላካዩ አህመድ ረሺድ አስደናቂ አቋም ታክሎበት ድሬዳዋ በርካታ ጎሎችን ከማስተናገድ የተረፈበትን ሂደት አስተውለናል። አዲስ ግደይ በሰጠው እና ሳይመን ፒተር ባመከናት ሙከራ ማጥቃታቸው የጀመሩት ንግድ ባንኮች ከቀኝ መስመር አቅጣጫ ወደ ውስጥ 77ኛው ደቂቃ ላይ የተሻማን ኳስ አስቻለው ታመነን ተክቶ ወደ ሜዳ የገባው ድልአዲስ ገብሬ ራሱ ላይ አስቆጥሮ አዲስ ግደይ ደግሞ ብረት ከመለሰበት ዕድል በኋላ በመጨረሻም ጨዋታው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

ወልዋሎ ዓ/ዩኒቨርስቲ 0-2 መቻል

በአሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት የሚመራው መቻል በመጀመሪያው አጋማሽ ጨዋታው ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር የቻለ ሲሆን ከአማካይ ክፍሉ ስርጭት ወደ መስመር አጋድሎ በሚደረግ እንቅስቃሴ ጎልን ያስቆጠሩት ገና አስረኛው ደቂቃ ላይ ነበር። ከአብዱልከሪም ያገኘውን ግሩም ሐጎስ ወደ ጎል ኳሷን ሲመታ መሐመድ አበራ አግኝቶ በቄንጠኛ አጨራረስ መረቡ ላይ አሳርፎ መቻል መሪ መሆን ችሏል። በእንቅስቃሴ ብልጫውን እየወሰዱ መጓዙን መርጠው የታዩት መቻሎች 36ኛው ደቂቃ በረከት ደስታ ቀኝ ሳጥን ቦታ ወደ ውስጥ ያሻማውን ኳስ ብሩክ ማርቆስ በግንባር ገጭቶ ሁለተኛ ጎል አድርጎታል።

በሁለተኛው አጋማሽ እጅግ ተሻሽለው ወደ ጨዋታ ለመመለስ በእጅጉ ጥረት ሲያደርጉ የታዩት ወልዋሎች ጥቂት የማይባል ዕድልን ማግኘት ቢችሉም ደካማ ከነበረው የአጨራረስ አቅማቸው አኳያ ከጎል ጋር ሊገናኙ ግን አልቻሉም። እንዳልካቸው ፣ ኮንኮኒ እና በየነ ባንጃው ተቀይረው ገብተው ጥራት የታከለባቸውን ሙከራዎች ቢያደርጉም ሳይሳካላቸው ጨዋታ በመቻል አሸናፊነት ተቋጭቷል።

You Might Also Like

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ

አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ

የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By hatricksport team
Follow:
Hatricksport team
Previous Article የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ባሳለፍነው ሳምንት በ ሁለት ከተሞች ጅማሮዉን አደረገ !
Next Article ወላይታ ድቻ አሰልጣኝ እና ስራ አስኪያጁን አሰናበተ

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ ቀናችን እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ
አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል

hatricksport team By hatricksport team 5 years ago
የጨዋታ ዘገባ | ሰበታ ከተማና ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል
“ለአፍሪካ ዋንጫ ሲባል የወንዶቹ ፕሪሚየር ሊጉ ተቋርጦ የለም ምነው ለሴቶቹ ሲባል ቅር አላችሁ?” አሰልጣኝ ፍሬው ኃ/ገብርኤል /የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ/
የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ጨዋታዎች /LIVESCORE/
ፍቅሩ ተፈራ የደቡብ አፍሪካው ማማሎዲ ሰንዳውንስ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ከባድ ፈተና ይጠብቃቸዋል ሲል አስጠነቀቀ፤”በጣም ዝነኛ፣ታላቅና ውጤታማ መሆኑ በራሱ ቅ.ጊዮርጊስ ምን አይነት ክለብ እንደሆነ ይናገራል።”
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?