መነሻ ገጽ ዜናዎች የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ባሳለፍነው ሳምንት በ ሁለት ከተሞች ጅማሮዉን አደረገ !
ዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግየጨዋታ ዘገባ

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ባሳለፍነው ሳምንት በ ሁለት ከተሞች ጅማሮዉን አደረገ !

አጋራ
አጋራ

በኢትዮጵያ ሁለተኛ የሊግ እረከን የሆነው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ ሀዋሳ ከተማ ፣ ምድብ ለ ደግሞ ጅማ ከተማ መደረገ የጀመረ ሲሆን በመጀመሪያ ሳምንት 12 ጎሎች መቆጠር ችሏል ።

የ የካ ተጨዋች የሆነ እንዳለ ደባልቄ የውድድሩን የመጀመሪያ ጎል ማስቆጠር የቻለ ሲሆን ቡድኑም በ ጭማሪ ሰዓት ባስቆጠሩት ጎል አሸናፊ መሆን ችለዋል በተቃራኒው የ አንደኛ ሊግ ሻምፒዮናውዎቹ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በሽንፈት ጀምረዋል ።

ጋሞ ጨንቻ አቃቂን ቤንቺማጂ ቡና ነቀምቴ ከተማን እና ንብ አዲስ አዳጊውን ሐረር ሲቲን ያሸነፉበት ፣ በሳምንቱ በምድቡ ያለግብ የተጠናቀቀው ጨዋታ ባቱ ከተማ ከ ሻሸመኔ ከተማ የተገናኙበት ጨዋታ በ ምድብ ሀ መደረግ ችሏል ።

በ አሰልጣኝ በሽር አብደላ የሚመራው እና በዘንድሮ የውድድር ዓመት እራሱን አጠናክሮ የቀረበው ሀላባ ከተማ በየውድድር ዓመቱ ብዙ ታዳጊዎችን የሚያስመለክተው ቦዲቲ ከተማ በጅማ የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ ጨዋታ ያደረጉ ሲሆን ያለ ጎል ባዶ ለባድ መለያየት ችለዋል ።

በላፈው የውድድር ዘመን ኔጌሌ አርሲን በመከተል ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የ አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ቡድን ደሴ ከተማ ውድድሩ በማሸነፍ ጀምሯል ።

በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በከፍተኛ ሊግ እየተሳተፍ የሚገኘው መንጌ ቤላሻንጉል የመጀመሪያ አንድነቡን ያገኘበት ጨዋታ ከ ሱሉልታ ከተማ ጋር ያለ ጎል ባዶ ለባዶ መጠናቀቅ ችሏል !!

ሁለቱ የአዲስ አበባ ቡድኖች የተገኙበት ጨዋታ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ከ አዲስ አበባ ከተማ ያለ ጎል ባዶ ለባዶ የተጠናቀቀ ሲሆን ሶሎዳ ዓድዋ ቢሾፍቱ ከተማን አንድ ለባዶ ማሸነፍ ችሏል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...