By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: ንግድ ባንክ እና ሀድያ ሆሳዕና የአዳማ ቆይታን በድል ጀምረዋል
Share
Notification Show More
Latest News
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና
አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
አርባምንጭ ከተማመቐለ 70 እንደርታሀዲያ ሆሳዕናየጨዋታ ዘገባየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎችኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ንግድ ባንክ እና ሀድያ ሆሳዕና የአዳማ ቆይታን በድል ጀምረዋል

hatricksport team
hatricksport team 3 months ago
Share
SHARE

የአዳማ ቆይታውን በሁለት መርሀግብር ዛሬ የጀመረው የሊጉ መርሀግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ሀድያ ሆሳዕናን በድል አስጀምሯል።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 3-1 አርባምንጭ ከተማ

የአዳማ ቆይታውን በሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ የጀመረው የአስረኛው ሳምንት መርሀግብር የተሻለ አጀማመርን ማድረግ የቻሉት ንግድ ባንኮች መሪ የሆኑበትን ጎል ያገኙትን ገና በጊዜ ነበር። 5ኛው ደቂቃ ላይ ለወትሮ ስህተት በማያጣው የአርባምንጭ ተከላካዮች በሳጥን ውስጥ ጥፋት የተሰራበት አምበሉ አዲስ ግደይ የተገኘችዋን የፍፁም ቅጣት ምት ራሱ ከመረብ አሳርፎ ክለቡን መሪ አድርጓል። በተጋጣሚያቸው በብዙ ረገድ ይበለጡ የነበሩት እና ወጥነት የሌለውን እንቅስቃሴን ሲያሳዩ የተስተዋሉት አርባምንጭ ከተማዎች በአጋማሹ አንድም ጥራት ያለው ሙከራን ሳያደርጉ ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል።

ከዕረፍት መልስ በቀጠለው እና አሰልጣኝ በረከትን ደሙን በቀጣዮቹ የሊጉ ጨዋታዎች ላይ ለመመልከት ወሳኝነቱ ከፍ ያለውን ቦታ የሚወስደው ሁለተኛው አጋማሽ 52ኛው ደቂቃ ላይ ቡጣቃ ሸመና ከጥሩ ቅብብል በኋላ ጎል በማስቆጠር ቡድኑን አቻ ማድረግ ቢችልም በቀጣዮቹ ደቂቃዎች ግን ወደ ጨዋታው በይበልጥ በመግባት ጫናን ማሳደር የቻሉት ንግድ ባንኮች 76ኛው ደቂቃ ላይ አዲስ ግደይ የሰጠውን ኳስ ሳይመን ፒተር ከመረብ ሲያሳርፍ 88ኛው ደቂቃ ላይ ደግሞ አዲስ ግደይ ከሳይመን ፒተር ያገኘውን ኳስ ለራሱ ሁለተኛ ለቡድኑ ሦስተኛ ጎል በማድረግ ጨዋታው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 3ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

- ማሰታውቂያ -

መቐለ 70 እንደርታ 1-2 ሀድያ ሆሳዕና

ሁለቱን የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸውን አሰልጣኞች ያገናኘው የምሽቱ መርሀግብር በቀዳሚው አጋማሽ ብልጫውን ለመውሰድ ጥረት ያደረጉት መቐለዎች እንደነበራቸው ብልጫ ጎልን 36ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥረዋል። ከማዕዘን ምት የተሻማች ኳስን በንክኪ ያገኘው ተከላካዩ ተመስገን ተስፋዬ ወደ ጎልነት ለውጦ የሰሜኑን ክለቡ ቀዳሚ አድርጓል። በመጀመሪያው አጋማሽ በብዙ ረገድ ኳስን መሠረት ባደረገ እንቅስቃሴ በወሰዱት ብልጫ ተጨማሪ ጎልን የማስቆጠር ዕድል የነበራቸው መቐለዎች ከዕረፍት ሲመለሱ ግን ተጋጣሚያቸው አሻሽሎ በገባው የጨዋታ መንገድ ጎሎችን ያስተናገዱበት ነበር።

ብሩክ በየነ በገጠመው ጉዳት ለተጨማሪ ህክምና ወደ ሆስፒታል ከሸኙ በኋላ የተጫዋቾች ለውጥን አድርገው በይበልጥ ወደ መስመር አጋድለው መጫወት የቻሉት ነብሮቹ 65ኛው ደቂቃ ከቅጣት ምት በተሻማ እና ተከላካዩ ቃልአብ ውብሸት እና የግቡ ቋሚ ብረትን ገጭታ የተመለሰች ኳስን ተመስገን ብርሀኑ በቀላሉ መረቡ ላይ በማስቀመጥ ቡድኑን 1ለ1 ማድረግ ችሏል። ተጨማሪ የማሸነፊያ ጎልን ለማግኘት በታታሪነት መጫወት የቻሉት ሀድያ ሆሳዕናዎች 76ኛው ደቂቃ ላይ ተመስገን ብርሀኑ እጅግ አስደናቂ ጎልን ለራሱም ለቡድኑም አክሎ ጨዋታውን ወደ 2ለ1 አሸጋግሯል። መደበኛውን የጨዋታ ደቂቃ ሊጠናቀቅ በቀረው ሰባት ደቂቃዎች ውስጥ የመቐለን ብቸኛ ጎል ያስቆጠረው ተመስገን ተስፋዬ በሰራው ጥፋት በዕለቱ ዳኛ ተፈሪ አለባቸው ሁለተኛ ቢጫ ተመዞበት በቀይ ካርድ ከሜዳ ከወጣ በኋላ ጨዋታው ተጨማሪ ጎል ሳናይበት ተቋጭቷል።

You Might Also Like

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ

አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ

የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By hatricksport team
Follow:
Hatricksport team
Previous Article ቅሬታ ያነሱት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አርቢትሮች የውሎ አበል ተጨመረላቸው….
Next Article አርባምንጭ ከተማ አሰልጣኙን አሰናበተ

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
ቅዱስ ጊዮርጊስየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዝውውር ዜናዎችዜናዎች

ፈረሰኞቹ የቀድሞ ግብ ጠባቂያቸውን አስፈርመዋል

Habtamu Mitku By Habtamu Mitku 1 year ago
በ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የዋንጫና የደረጃ ጨዋታዎች የዳኞችና የታዛቢዎች ሪፖርትን በመመልከት የተላለፉ ውሳኔዎች
“በጣት የሚቆጠሩ ግለሰቦች እያደረጉ ያሉትን ዘመቻ ደርሰንበታል ” ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻው
የአፍሪካ እግር ኳስ እና ወቅታዊው ኮሮና ቫይረስ !
የጨዋታ ዘገባ| በቀጣይ አመት የትግራይ ክልል ከለቦች የማይሳተፋ ከሆነ በሊጉ የሚሳተፈዉ አንዱ ክለብ አዳማ ከተማ መሆኑ ታዉቋል!
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?