ወቅታዊውን የኑሮ ሁኔታ ታሳቢ ያላደረገ ነው በሚል የፕሪሚየር ሊጉ ዳኞችያነሱት ቅሬታ ምላሽ ማግኘቱ ተሰምቷል።
*…. ፊፋ የኢንተርናሽናል ዳኞችን ዝርዝር አሳውቋል።
የሊጉ ዳኖች ሲያጫውቱ የሙያ አበል 3 ሺህ ብር የውሎ አበል ደግሞ 2 ሺህ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን ውድድሩ ከ5 አመት በኋላ ወደ አዲስ አበባ ሲመለስ ወቅታዊውን የኑሮ ሁኔታ አላማከለም በሚል ዳኞቹ ቅሬታ ሲያሰሙ መቆየታቸው ታውቋል።
የአርቢትሮቹ ቅሬታ የደረሳቸው የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ የጥያቄውን ተገቢነት በመቀበል ከፕሪሚየር ሊጉ አክሲዮን ማህበር አመራርች ጋር ከተወያዩ በኋላ ማሻሻያ ተደርጓል።
- ማሰታውቂያ -
ፕሬዝዳንቱ ከሊግ ኩባንያው አመራሮች ጋር ከመከሩ በኋላ የሙያ አበሉ የ3ሺሄ ብር ክፍያ ባለበት እንዲቀጥል የውሎ አበሉ 2 ሺህ ክፍያ ላይ 1500 ብር እንዲጨመር ተስማምተው ከ8ኛው
ሳምን ጀምሮ ተግባራዊ መደረጉ ታውቋል።
ሁለቱ ወገኖች ባደረጉት ውይይት ዳኞች በመኖሪያ ከተማቸው ሲመደቡ የውሎ አበል የማይከፈላቸው የነበረ ሲሆን አሁን ግን ግማሹን 1, 750 ብር ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲከፈላቸው መደረጉ ፕሬዝዳንቱ አቶ ኢሳያስ ጅራን አስመስግኗል።
በሌላ በኩል ፊፋ የአዲሱን አመት የኢንተርናሽናል ዳኞችን ዝርዝር ይፋ አድርጓል።
በዚህ መሰረት በወንዶች አራት ዳኞች ማለትም ዳንኤል ይታገሱ፣ ሄኖክ አበበ፣ ሃይማኖት አዳነና ባህሩ ተካ በሴት አንድ ዳኛ ዮርዳኖስ ሙሉጌታ ፣ በወንድ ረዳት ዳኛ አራት ሲራጅ ኑርበገን፣ ዘመኑ ሲሳይነው፣ አማን ሞላ እና ኤልያስ መኮንን እንዲሁም በሴት ረዳት አንድ መቅደስ ብርሃኑ በአጠቃላይ 10 የጨዋታ አመራሮች በአዲስ መልክ መተካታቸውን ፊፋ መቀበሉን ለፌዴሬሽኑ አሳውቋል።
በተጨማሪም ለ5 ዓመታት ተቀንሶ የቆየው የአንድ የረዳት ዳኛ ኮታ ወደነበረበት እንዲመለስ በመወሰኑ የረዳት ዳኛም ኮታ 7 መሆኑ ታውቋል።


