By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: የ10ኛው ሳምንት ቀዳሚ የአዲስ አበባ ጨዋታ ያለ ግብ ተጠናቋል
Share
Notification Show More
Latest News
ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ
ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና
“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና
አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎችባህርዳር ከተማየጨዋታ ዘገባሽረ ምድረገነት

የ10ኛው ሳምንት ቀዳሚ የአዲስ አበባ ጨዋታ ያለ ግብ ተጠናቋል

Habtamu Mitku
Habtamu Mitku 3 months ago
Share
SHARE

ባህርዳር ከተማ እና ምድረ ገነት ሽረ ነጥብ ተጋርተዋል

የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በዛሬው ዕለት መደረግ ሲጀምሩ አዲስ አበባ ስታድየም ላይ የተደረገው የባህርዳር ከተማ እና ምድረ ገነት ሽረ ጨዋታ 0 ለ 0 ተጠናቋል።

በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ባህርዳር ከተማዎች የተሻለ በመንቀሳቀስ በኳስ ቁጥጥር እና ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል በመድረስ ረገድ ከምድረ ገነት ሽረ የተሻለ ጊዜን አሳልፈዋል።

ደጋግመው የምድረ ገነት ሽረን የኋላ ክፍል የፈተኑት የጣና ሞገዶቹ የጠራ የግብ ዕድል ለመፍጠር ግን ደቂቃዎችን መታገስ የግድ ብሏቸው ነበር።

- ማሰታውቂያ -

በ24ኛው ደቂቃ ላይ ወንድወሰን በለጠ ከአማኑኤል ገብረሚካኤል የደረሰውን ኳስ ወደ ምድረ ገነት ሽረ ሳጥን ይዞ ገብቶ ለማስቆጠር ቢጥርም በአዲስ ተስፋዬ ጫና እና በሪችሞንድ አይ ጥረት ሳይቆጠር ቀርቷል።

መደበኛው የመጀመሪያ አጋማሽ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ በተጨማሪ ደቂቃዎች ላይ ሔኖክ ይበልጣል ከቅጣት ምት የተነሳን ኳስ አግኝቶ ወደ ግብ ያደረገውን ጠንካራ ሙከራ ሪችሞንድ አይ አውጥቶታል።

በምድረ ገነት ሽረ በኩል ወደ ሳጥን በሚላኩ ኳሶች የግብ ዕድሎችን ለመፍጠር ቢጥሩም ፔፔ ሰይዶን የፈተነ ሙከራ ሳያደርጉ የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል።

በሁለተኛው አጋማሽ 66ኛ ደቂቃ ላይ ባህርዳር ከተማዎች መሪ መሆን የሚችሉበትን ዕድል አግኝተው ነበር።

አማኑኤል ገብረሚካኤል ወደ ግብ ያደረገውን ሙከራ ስንታየሁ ወለጪ በዕጁ መመለሱን ተከትሎ የተሰጠውን የፍፁም ቅጣት ምት መሳይ አገኘሁ ቢመታውም ሪችሞን አይ አድኖታል።

ተደጋጋሚ ጫና ማሳደራቸውን የቀጠሉት ባህርዳር ከተማዎች በ74ኛው ፣ 76ኛው እና 92ኛው ደቂቃዎች ላይ ወደ ግብ የቀረቡባቸውን ሙከራዎች ማድረግ ቢችሉም ኳስ እና መረብን ግን ለማነገናኘት አልቻሉም።

የባህር ዳር ከተማ ዋና አሰልጣኝ ደግአረግ ይግዛው ከጨዋታው በኋላ በሰጡት አስተያየት እንደነበረን ብልጫ አሸንፈን መውጣት ይገባን ነበር ሲሉ ተናግረዋል።

ቡድናቸው ለማሸነፍ የነበረውን ጥረት ያደነቁት አሰልጣኙ ነገር ግን ያ ጥረት በቂ አለመሆኑ ሶስት ነጥብ ይዘው እንዳይወጡ እንዳደረጋቸው ገልጸዋል።

አሁን ላይ ግብ ጠባቂ የቡድን 75 በመቶ ነው ያሉት የምድረ ገነት ሽረው አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ በበኩላቸው የሪችሞንድ አዬ ብቃት በጨዋታው አስደናቂ እንደነበር ጠቅሰዋል።

ኳሶችን ከመሀል ሜዳ ተጫዋቾች ወደ መስመር ተጫዋቾች በማድረስ ለማጥቃት አቅደው ስለመግባታቸው የተናገሩት አሰልጣኙ ነገር ግን መረጋጋት አለመኖሩ ቡድናቸው ያሰበውን አሳክቶ እንዳይወጣ እንዳደረገው ተናግረዋል።

በ11ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ እንዲሁም ባህርዳር ከተማ ከፋሲል ከነማ ይጫወታሉ።

You Might Also Like

ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ

“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Habtamu Mitku
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article ቅዱስ ጊዮርጊስ የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ተፈራረመ።
Next Article ቅሬታ ያነሱት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አርቢትሮች የውሎ አበል ተጨመረላቸው….

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎችቅዱስ ጊዮርጊስአርባምንጭ ከተማየጨዋታ ዘገባቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ

የጨዋታ ዘገባ | ፈረሰኞቹ ሊጉን መምራታቸውን ቀጥለዋል !!

Ermias Misganaw By Ermias Misganaw 4 years ago
​በኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ከ ሲዳማ ቡና ነጥብ ተጋርተው ወጠዋል
ጉዳፍ ፀጋይ የ1500 ሜትር የአለም ክብረወሰንን ስታሻሽል ሌሎች አትሌቶችም ድል ቀንቷቸዋል
“ህልሜን እየኖርኩ ነው” “ቡድናችን በጥሩ መነቃቃት ላይ ነው” “ለእግር ኳስ የተለየ ፍቅር ካለው ማህብረሰብ ውስጥ በመፈጠሬ ዕድለኛም ደስተኛም ነኝ” “የውጤታማነታችን ሚስጥር አንድነታችን ነው” “ክለቦች ወጣት ቡድኖቻቸው ላይ በደንብ ትኩረት ሰጥተው መስራት አለባቸው” ብሩክ ማርቆስ (ሀዲያ ሆሳዕና)
የጨዋታ ዘገባ | ዋልያዎቹ እና ጥቋቁር ከዋክብቶቹ በአምበሎቻቸው ግቦች አቻ ተለያይተዋል
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?