መነሻ ገጽ አርባምንጭ ከተማ አርባምንጭ ከተማ አሰልጣኙን አሰናበተ
አርባምንጭ ከተማዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

አርባምንጭ ከተማ አሰልጣኙን አሰናበተ

አጋራ
አጋራ

አሰልጣኝ በረከት ደሙ ከአርባምንጭ ከተማ ጋር ሲለያዩ የቀድሞው አንጋፋ ተከላካይ ቡድኑን ተቀላቅሏል።

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ደካማ የውድድር ጉዞን እያደረጉ ከሚገኙ ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው አርባምንጭ ከተማ ትላንት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡድኑ መረታቱን ተከትሎ ለአሰልጣኝ በረከት ደሙ ከሳምንታት በፊት የሰጠውን የሦስት ጨዋታዎች ዕድል ባለ መጠቀሙ ክለቡ ማሰናበቱን የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት ሀይለማርያም አረጋግጠውልኛል።

በሊጉ ከተደረጉ አስር ጨዋታዎች አምስት ተሸንፎ በአምስቱ አቻ ወጥቶ አንድም ጨዋታ ማሸነፍ ሳይችል በ5 ነጥብ በደረጃ ሰንጠረዡ 19ኛ ላይ ለመቀመጥ የተገደደው ክለቡ ለጥቂት ጨዋታዎች ቦቻ ቦታውን በጊዜያዊ የአሰልጣኝነት ማዕረግ አዲስ አሰልጣኝ እስኪሾም ድረስ የቀድሞው የአርባ ምንጭ ጨርቃጨርቅ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ የሱዳኑ አልሀሊ ሸንዲ ፣ ደቡብ ፓሊስ ፣ ወልቂጤ ከተማ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የግራ መስመር ተከላካይ እና በቅርቡ የፋስት ትራክ የቢ ላይሰንስ ባለቤቱ አበባው ቡጣቆ ቡድኑን በጊዜያዊ ስያሜ አሰልጣኝ (ማስተባበር) ስራን እንዲመራ ተመርጧል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...