የፈረሰኞቹ ግብ ጠባቂ የመኪና አደጋ ደረሰበት !

ያለፉት ዓመታት የ ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ግብ ሲጠብቅ የቆየው ፓትሪክ ማታሲ የመኪና አደጋ እንደ ደረሰበት የተለያዩ የአፍሪካ መገናኛ ብዙሀን እየዘገቡ ይገኛሉ ።

ማታሲ የመኪና አደጋው በ ካፓሳቤት ናኩሩ ጎዳና ላይ አደጋው ሲከሰትበት በፍጥነት በስፍራው ወደ ሚገኘው ካፓሳቤት ሆስፒታል መወሰዱ ተገልጿል ።

ማታሲ መኪናውን እያሸከረከረ እንደነበረ ሲገለፅ ከመኪናው ጎማ ጋር በተያያዘ ችግር መቆጣጠር አቅቶት አደጋው ሊከሰት እንደተቻለ ተጠቁሟል ።

ማታሲ ከ ሁለት ወንድሞቹ ጋር እንደነበረ ሲገለፅ በአሁን ሰዓት የደረት ህመም እንደሚሰማው ለማወቅ ተችሏል ።

ማታሲ በትላንትናው ዕለት የቀድሞው ክለቡን ተስካር እግር ኳስ ክለብ ከሜዳው ውጪ ያሸነፈበትን ጨዋታ መታደም ችሎ ነበር ።

ማታሲ ሊጉ መገባደደቡን ተከትሎ ያሳለፍነው ቅዳሜ ረፋድ ላይ ከ አዲስ አበባ ወደ ኬንያ አቅንቶ ነበር ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor