ለሃዋሳው የእግርኳስ ፍልሚያ 12 አርቢትሮች ተመርጠዋል

በወልቂጤ ከተማ ፣ በአዳማ ከተማ ፣ በጅማ አባጅፋር፣ በኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ በኮልፌ ክ/ከተማና አምበሪቾ ክለቦች መሃል ሀዋሳ ላይ ለሚጀመረው ሻምፒዮና ብሄራዊ አርቢትሮች ኮሚቴ 12 አርቢትሮችን መምረጡ ታውቋል።

ወልዋሎ አዲግራት፣ መቀለ 70 እንደርታና ስዑል ሽረ የማይመጡ ከሆነ እነሱን ተክቶ በ2014 የፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ለመሆን ለሚደረገው የማጣሪያ ውድድር ስድስት ዋናና ስድስት ረዳት ዳኞች ተመርጠዋል።

የፊታችን አርብ ለሚጀምረው ውድድር በሀዋሳው የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዎች ያልተመደቡት ፌዴራል አርቢትር ዳንኤል ግርማይና ኢንተርናሽናል አርቢትር ሊዲያ ታፈሰን ጨምሮ የአመቱ የፕሪሚየር ሊጉ ኮከብ ኢንተርናሽናል አርቢትር በላይ ታደሰና ኢንተርናሽናል አርቢትር ሃ/የሱስ ባዘዘው ተካተውበታል።

ከዚህም በላይ የአመቱ ኮከብ ተብሎ የተመረጠው ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ተመስገን ሳሙኤልን ጨምሮ ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ትግል ግዛው፣ ኢንተረናሽናል ረዳት ዳኛ ክንዴ ሙሴና ፌዴራል ረዳት ዳኛ ዳንኤል ጥበቡ ተካተውበታል።

በዚህ መሰል ወሳኝ የማጣሪያ ውድድሮች ላይ የተለመደው የሙስናና የጨዋታ ማጭበርበር እንዳይከሰትበት የኢትዮዽያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከፍተኛ ጥረት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport