” አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ እንኳን ደስ አለህ ሶስት ነጥቡ ላይ አለህበት ” አቶ ኢሳያስ ጅራ
በአሁን ሰዓት በ ኢንተር ኮንትኔንታል ሆቴል የመጀመሪያውን ዙር የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ መገባደድ ተከትሎ የመጀመሪያው ዙር ግምገማ እና ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል ።
የዕለቱ የክብር እንግዳ ሆነው የተገኙት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ በዕለቱ በስፋራው በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ማድረግ ሲችሉ የተለያዩ ሀሳቦችን አንስተዋል ።
በመክፈቻ ንግግራቸውም “በ ብሄራዊ ቡድኑ ድል ተደስተናል ፣ ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ከጫፍ ደርሰናል ።
አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ እንኳን ደስ አለህ ሶስት ነጥቡ ላይ አለህበት ፣ ክለቦች የናንተም አስተዋጽኦ አለበት እና እንኳን ደስ አላችሁ ” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ።
አቶ ኢሳያስ ጅራ ከዚህ ባለፈም ከመጪው ሀምሌ ወር ጀምሮ በ ፌዴሬሽኑ አዘጋጅነት ከ 17 ዓመት በታች ውድድር እንደሚጀመር ተናግረዋል።
በፕሪምየር ሊጉ ላይ የሚወዳደሩ አስራ ሦስቱም ክለቦች በግዴታ ክለብ እንዲይዙ እንደሚደረግ አስታውቀዋል። አቶ ኢሳያስ ጅራ አያይዘውም ክለቦች በትክክለኛው የእድሜ እርከን ተጫዋቾችን እንዲያዋቅሩ አሳስበዋል።