” የሊጉ ጨዋታዎች አሁን ባለው የቫይረሱ ስርጭት ሊቋረጥ ይችላል ” መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አ.ማ በ ቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በተካሄዱ 16 ሳምንት ጨዋታዎች ዙሪያ በአሁን ሰዓት በ ኢንተር ኮንትኔንታል ሆቴል ግምገማ እና ውይይት እየተካሄደ ይገኛል ።

በ አክሲዮን ማህበሩ ፕሬዚዳንት መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ የመክፈኛ ንግግር የተጀመረው የዕለቱ መርሐ ግብር ከፍተኛ ማስጠንቀቂያን ሰጥተዋል ።

መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ በመክፈቻው ንግግር እንደተናገሩት ሊጉ በቀጣይ የሚደረግባቸው ከተሞች ድሬደዋ እና ሀዋሳ በሀገሪቱ በአሁኑ ወቅታዊ የኮቪድ ቫይረስ ከፍተኛ ቁጥር የሚያስመዘግቡ ከተሞች መሆናቸውን አሳስበው ክለቦች ተጫዋቾቻቸውን ለሻይ እና ለሽርሽር መውጣት መከልከል እንዳለባቸው አሳስበዋለው ።

” ለሻይ ለሽርሽር ብላችሁ ከሆቴላቸው እንዳይወጡ ብርቱ ማሳሰቢያ መስጠት እንፈልጋለን ፣ የሊጉ ጨዋታዎች አሁን ባለው የቫይረሱ ስርጭት ሊቋረጥ ይችላል ይህ ደግሞ እንዲሆን አንፈልግም ” ሲሉ በሰጡት አስተያየት አሳስበዋል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor