ግዙፉ የጅማ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ለማስተናገድ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል።
የመጀመሪያ ዙር የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከሚያስተናግዱት ስታዲየሞች መካከል አንዱ የሆነው የጅማ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም ሲሆን የሀገሪቱን ትልቅ ውድድር የሆነው የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ከ ሰባተኛው እስከ አስራ አንደኛው ሳምንት ያሉ ጨዋታዎችን ለማዘጋጀት ዕድሉን አግኝቷል።
ተሳታፊ የሆኑት የሊጉ ክለቦች ከ ቅዳሜ ጀምሮ ወደ ጅማ መግባት የጀመሩ ሲሆን አሁን ላይ ሁሉም ክለቦች ካምፓቸውን አዘጋጅተው የጅማ ከተማ ዋናው ሜዳን ጨምሮ በሌሎች በተለያዪ በተዘጋጀላቸው የመለማመጃ ሜዳ ልምምዳቸውን እያደረጉ ይገኛሉ።

ጨዋታውን በቀጥታ ቴሌቪዥን የሚያሰራጨው የሱፐር ስፖርት የቡድን አባላትም ጅማ ከተማ የገቡ ሲሆን የመጫወቻ ሜዳውም ሙሉ ለሙሉ ለጨዋታ ዝግጁ እንደሆነ ሀትሪክ ስፖርት ድህረገጽም በስፍራው ተገኝታ ለማረጋገጥ ችላለች ።
ሆኖም ጨዋታውን በቀጥታ የሚያስተላልፈው የ ዲ ኤስ ቲቪ የቴሌቪዥን ተንቀሳቃሽ መኪናም ከጉምሩክ ጋር በተያያዘ ችግር ዘግይቶ ዛሬ ከሰዓት ከአዲስአበባ ወደ ጀማ ያመራ ሲሆን ማምሻውን ቦታው ላይ በመገኘት ለነገው ጨዋታ ዝግጅታቸውን እንደሚያጠናቅቁ ይጠበቃል ።
አስተያየት ይስጡ