ቁጥራዊ መረጃዎች በዛሬው ጨዋታ

የፈረሰኞቹ የፊት መስመር አጥቂ ሳላህዲን ሰዒድ ከ 307 ቀናት በኋላ የመጀመሪያ ጨዋታውን በዛሬው ዕለት አድርጓል ።

• ሳላህዲን ሰዒድ ለፈረሰኞቹ ለመጨረሻ ጊዜ የተጫወተው የነበረው በ አስራ ሰባተኛው ሳምንት ከ ሰበታ ከተማ ጋር ሲያካሂድ ከሜዳ በቀይ ካርድ መውጣቱ ይታወሳል ።

• ጌታነህ ከበደ ለፈረሰኞቹ ሀትሪክ ሲሰራ በውድድር ዓመቱ ሰባተኛ ጎሉን በማስቆጠር በኮከብ ግብ አግቢነት ተፎካካሪነቱን ተቀላቅሏል ።

• ጌታነህ ከበደ በኮሮና ቫይረስ በተቋረጠው አስራ ሰባት ሳምንታት የውድድር ዓመት ካስቆጠረው የግብ መጠን ስድስት ከወዲሁ በአንድ ከፍ ብሎ መቀመጥ ችሏል ።

• ጅማ አባ ጅፋርን ቀዳሚ ያደረገች ግብ ከርቀት ማስቆጠር የቻለው ሮባ ወርቁ በተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ግብ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል ።

• ጌታነህ ከበደ ሀትሪክ መስራቱን ተከትሎ በውድድር ዓመቱ ከ ሙጂብ ቃሲም እና አቡበከር ናስር በመቀጠል ሶስተኛው ሀትሪክ ሰሪ ለመሆን ችሏል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor