ለጅማ አባጅፋር የፈረመው የዮሃንስ ሽኩር ውል አየር ላይ ታፈነ…

 

ፌዴሬሽኑ ክለቡን ማብራሪያ ጠይቋል

ለኢትዮጲያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የገባ የዮሀንስ ሽኩርና የጅማ አባጅፋር ውል የገባበት አልታወቀም….ግን ፈርሟል።
የክለቡ ተጨዋቾች ውል በክለቡ ጉዳይ ፈጻሚ አቅራቢነት በወ/ሮ ዘውድነሽ ይርዳው አማካይነት ፊርማው ከተከናወነ በኋላ ወደ ዋና ጸሃፊው አቶ ባህሩ ጥላሁን ቢሮ ገብቶ እንዲጸድቅ ይደረጋል። ግብ ጠባቂው ዮሀንስ ከፊርማው በፊትም ሆነ በኋላ ከክለቡ ተጨዋቾች ጋር ለወር ያህል ልምምድ ሲሰራ ቆይቷል ትላንት ደርሶ የዝውውር መስኮቱ ከተዘጋ ቀናት በኋላ የቡድኑ ምክትል አሰልጣኝና የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ “ክለቡ በጀት የለውምና አብረን መቀጠል አንችልም እናዝናለን”እንዳሉት ተጨዋቹ ይናገራል..
ውል እንዳለው የሚያውቀው ዮሀንስ ፌዴሬሽን ሲሄድ የገጠመው ሌላ ነው።
ውሉ የለም..ወይዘሮ ዘውድነሽን ጨምሮ ሁሉም እንደፈረመ ግን ያውቃሉ…ዋና ጸሃፊው ቢሮ ሲፈለግ የርሱና የአንድ ተጨዋች ውል የለም ፌዴሬሽኑ ለክለቡ በሁለት ቀን ውስጥ ማብራሪያ እንዲሰጠው በደብዳቤ ጠይቋል።

ጉዳዩ በክለቡና በፌዴሬሽኑ መሃል ያለውን መተማመን የሚጎዳ ነው ሲልም አስጠንቅቋል። ከአይቲ ዲፓርትመንት ወደ ዋና ጸሃፊው ቢሮ የሄደው ውል መሃል ላይ ማን አፈነው..?ተጨዋቹ ግን”በጣም አዝኛለሁ የዝውውር መስኮቱ ተዘግቷል ምን ማድረግ ይቻለኛል ከፌዴሬሽኑ ፍትህ እጠብቃለሁ ይህ ግፍ ነው በፍጹም የምተወው ጉዳይ አይደለም”ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል። የክለቡ አመራሮች መሃል አንዱ የሆኑት አቶ አጃይብ አባሜጫ ግን “ምንም መረጃ የለኝም ለማጣራት እሞክራለሁ”ሲሉ ተናግረዋል።

 

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport