በ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ላይ ውሳኔዎች ተላለፉ !

 

የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ውድድር አመራር እና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ በትላንትናው ዕለት ባደረገው ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን ማስተላለፉ ይፋ ሆኗል ።

ከተላለፉ ውሳኔዎች መካከል የወልቂጤ እግር ኳስ ክለብ የተጫዋቾች ተገቢነት ክስ በጅማ አባ ጅፋር ክለብ ላይ ያቀረበ መሆኑን ተከትሎ ጉዳዩ ከ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ ውጤቱ ያልፀደቀ መሆኑ ይፋ ተደርጓል ።

የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሶስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከነገ ጀምሮ ሲካሄዱ ሰላሳ ሁለት የቢጫ ካርዶች በሁለቱ ሳምንታት በዳኞች ሲመዘዙ አስራ ሰባት የሚሆኑት ከ ስፖርታዊ ጨዋነት ውጪ በሆኑ አጋጣሚዎች ላይ የተሰጡ መሆናቸው ተገልጿል ።

በታያየዘ መረጃ የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ በሁለተኛው ሳምንት በተሰጠ ነጥብ 9.50 በማግኘት የስፖርታዊ ጨዋነት ደረጃን በመጀመሪያ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሀድያ ሆሳዕና እና ኢትዮጵያ ቡና በ 8.00 ነጥብ የመጨረሻዎቹን ደረጃ መያዛቸው ታይቷል ።

በመጀመሪያው ሳምንት የስፖርታዊ ጨዋነት ደረጃ ኢትዮጵያ ቡና እና ባህርዳር ከተማ ከፍተኛ ነጥብ 9.75 በማምጣት ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዙ በተቃራኒው ቅዱስ ጊዮርጊስ 7.75 ነጥብ በመያዝ የመጨረሻውን ስፍራ ይዘው ነበር ።

በሁለተኛው ሳምንት የቀይ ካርድ መመልከት የቻለው የ ኢትዮጵያ ቡናው ተመስገን ካስትሮ የሶስት ጨዋታዎች ቅጣት እና የ 3,000 ብር የገንዘብ መቀጮ እንደተጣለበት ተገልጿል ። ከዚህ በተጨማሪም የወላይታ ድቻው አናጋው ባደግ በቀጣይ ከ ወልቂጤ ከተማ ጋር የሚደረገው አንድ ጨዋታ የሚያመልጠው መሆኑ ተነግሯል ።

በተለያዩ ምክንያቶች ባለፉት ሳምንታት የማስጠንቀቂያ ካርድ የተመለከቱ ተጫዋቾች እያንዳንዳቸው የ 5,000 ብር መቀጮ እንደተቀጡ እና ውሳኔ በደረሳቸው ሰባት ቅናት ክፍያ መፈፀም እንዳለባቸው በአንክሮ ተገልጿል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor