” ወደ ሀዋሳ የተመለስኩበት ምክንያት በአሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት ነው ” ኤፍሬም ዘካርያስ /ሀዋሳ ከተማ/

በትውልድ ከተማው መተሐራ እግር ኳስን የጀመረው የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና ፤ሀዋሳ ከተማ ፤ የአዳማ ከተማ እና የአሁኑ የሀዋሳ ከተማ አማካይ ኤፍሬም ዘካሪያስ ስለ ዘንድሮው የውድድር ፣ ስለ ሀዋሳ ከተማ ፣ ስለ ሙሉጌታ ምህረት እና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ሀትሪክ ስፖርቱ ፀሀፊ ቅዱስ ዮፍታሔ ጋር ቆይታን አድርጓል።

የሀዋሳ ከተማ የዘንድሮ አቋም . . . . . . .

ጥሩ ነው ብዬ አስባለው አንድ አንድ ጨዋታዎች ላይ እንደ ቡድን ወርደን የቀረንባቸው አጋጣሚዎች ግን ደረጃችንን ወደ ፊት እንዳናሳድግ አድርገውናል ። ከ ሞላ ጎደል አሁን ላይም ቢሆን የምንገኝበት ሁኔታ ጥሩ ሲሆን ወደ ደረጃ ሰንጠረዡ በላይ ለመውጣት የሚያስችል አቅም አለን ።

በቀጣይ ባለን ጊዜ እንደ ቡድን ማስተካከል ያሉብንን ነገሮች ላይ በመስራት ክፍተቶቸቻችንን አስተካክለን በ ባህርዳሩ ውድድር ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ በመሆን ከዚህ የተሻለ ቡድንን ይዘን እንቀርባለን ።

የቡድናችን ጥሩ ጎን እንደ ቡድን በህብረት መስራታችን ጠንካራው ጎናችን ነው ብዬ አምናለው ፣ ማስተካከል አለብን ብዬ የማስበው ነገር የግብ እድሎችን መፍጠር ላይ መሻሻል እንዳለብን ይሰማኛል ።

የ ዲ ኤስ ቲቪ መምጣት . . . . . . . .

ዲኤስቲቪ መምጣቱ ለሊጋችን በጣም ጥሩ አጋጣሚ ሆኖልናል ፣ ለእያንዳንዳችን ተጫዋቾች የራሳችን ጨዋታ እያየን ክፍተቶቻችንን እንዲሁም ማረም ያሉብንን ነገሮች እንድናርም ይረዱናል ። ከእኛ ከተጫዋቾችን ባለፈም ለስፖርት ቤተሰቡም ቢሆን ጥሩ አጋጣሚ ነው ፣ የተጫዋቾችን ብቃት ለማየት ይረዳቸዋል ። ከዚህ ባለፈ ግን አቅም ላላቸወው ታዳጊ ተጫዋቾች ትልቅ መነሳሳትን ይፈጥርላቸዋል ብዬ አሳብለው ።

ስለ አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት . . . . . . . .

ከ ሙሌ ጋር የመጨረሻዎቹ ኳስ ከማቆሙ በፊት ባሉት ጊዜው አብሮ የመጫወቱን እድል ማግኘት ችዬ ነበር ፣ በዚህም እራሴን በጣም እድለኛ አድርጌ እቆጥረዋለሁ ።

በአሰልጣኝነቱ በጣም ለተጫዋቾች ቅርብ ነው ፣ እንደ ጓደኛም እንደ ታላቅ ወንድምም ነው ለኛ ። ወደ ሀዋሳ ዳግም የተመለስኩበትም ምክንያት በእርሱ ስር ለመስራት ካለኝ ፍላጎት ነው ። የዘንድሮው የውድድር ዓመት በአሰልጣኝነቱ የመጀመሪያው ዓመቱ ቢሆንም ባለነው ልጆች ላይ ለመስራት እያሰበ ያለው ነገር ትልቅ ነው ።

ከ ሀዋሳ ክለብ አመራሮች ትልቅ እገዛን ቢያገኝ ከዚህ በላይ መስራት ይችላል ፣ በቀጣይ አመት ጎበዝ እና ትልቅ አቅም ያለው አሰልጣኝ እንደሚሆን አምናለው ። ለእኛ ለተጫዋቾች ባለው እና በሚሰጠው ክብር ላመሰግነው ስወድ የተሻለ ስኬትን ከወዲሁ እመኝለታለሁ ።

የሀዋሳ ከነማ የቡድን ስብስብ . . . . . . . .

ስብስባችን ከተከላካይ በስተቀር አብዛኞቹ ታዳጊዎች ናቸው ። መሐል ላይ ደግሞ እየተሰለፍን ካለነው እኔ ብቻ ነኝ ልምድ ያለኝ ፣ ስለዚህም ብዙ ስራ መስራት ይጠበቅብኛል ፣ ይሄንን ለማድረግ ደግሞ ብዙ እየጣርኩ እግኛለሁ ።

ታዳጊዎች ስለሆኑ ከጨዋታ ጨዋታ እየተሻሻሉ ነው ፣ ሁሉም በቀጣይ ልምዱን እያገኙ ሲሄዱ ከታዳጊዎች ብዙ እንጠቀማለን ብዬ አስባለው ።

በሁለተኛው ዙር ብዙ ማስተካከያ ጊዜ ስለሚኖረን ያሉብንን ችግሮች ሰርተን አስተካክለን እንመጣለን ። በ አሰልጣኞችም በኩል ቢሆን የሚጨመሩ ተጫዋቾች ለማስተካከል ይሞክራሉ የሚል እምነት አለኝ ። ይህ የማይሆን ከሆነም ባለን ስብስብ ማሰተካከል ያሉብንን ክፍተቶች በመቅረፍ እንቀርባለን ።

ዘንድሮ ሊጉ ከባድ ነው ፣ ሀዋሳ ከነማ ደግሞ ትልቅ ክለብ እና ትልቅ ስም ያለው ክለብ ስለሆነ ያሉትን ችግሮች ለማስተካከል የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን ። ዘንድሮ ፉክክሩ ከበድ ይላል ፣ አሁንም ቢሆን ጊዜው ገና ነው ስለዚህ እያንዳንዱን ጨዋታ በትኩረት የሚጫወት ቡድን ውጤታማ ይሆናል ብዬ አስባለው ።

ስለ ማጥቃት አማራጫቸው ብሩክ በየነ እና መስፍን ታፈሰ . . .

ብሩክ በየነ እና መስፍን ታፈሰ ጎበዝ እና ከዚህ በላይ አቅማቸውን አውጥተው ሀዋሳን ስኬታማ ቡድን ያደርጋሉ ብዬ አስባለው ። አሁንም በማጥቃቱ ረገድ ሙሉ በሙሉ እነሱን ስለምንጠቀም ጎሎችን ከእነርሱ እያገኘን ነው ያለነው ፣ ቢሆንም ግን እነርሱ በሚያገቡት ጎል ብቻ ሀዋሳ አሸናፊ አይሆንም ፣ እንደ ቡድን ያለን ነገር አሸነፊ እያደረገን ይገኛል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor