ጉዳፍ ፀጋይ የ1500 ሜትር የአለም ክብረወሰንን ስታሻሽል ሌሎች አትሌቶችም ድል ቀንቷቸዋል

 

ጉዳፍ ፀጋይ በሌቪን ፈረንሳይ በተካሄደ የ1500 ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር አዲስ የአለም ክብረወሰን አስመዘገበች።

አትሌቷ በፈረንጆቹ 2014 አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በካርልስሩህ ያስመዘገበችውን ክብረወሰን በ2 ሰከንድ በማሻሻል ርቀቱን በ3:53.09 ማጠናቀቅ ችላለች።

አትሌት ለምለም ሀይሉም በዚሁ የፈረንሳይ የቤት ውስጥ ሻንፒዮና ውድድር በ3000 ሜትር 8:32,55 በመሮጥ ስታሸንፍ፣ አትሌት ሀብታም አለሙ በ800 ሜትር 2:00;86 በመሮጥ 2ኛ ሆናለች።

በዚሁ የቤት ውስጥ ውድድር በ3,000 ሜትር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1-4ኛ መውጣት ችለዋል፡፡

በዚሁ መሰረት አትሌት ጌትነት ዋለ1ኛ፣ ሰለሞን ባረጋ 2ኛ፣ ለሜቻ ግርማ 3ኛ ፣ በሪሁ አረጋዊ 4ኛ፣ ታደሰ ወርቁ 6ኛ በመሆን ጨርሰዋል፡፡

 

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *