“ሲዳማ ቡናን ማሸነፋችን ወደ ዋንጫው የሚወስደንን ጉዞ ይበልጥ አሳምሮልናል”

“ሲዳማ ቡናን ማሸነፋችን ወደ ዋንጫው የሚወስደንን ጉዞ ይበልጥ አሳምሮልናል”

“በኮቪድ የተያዝኩትና በህክምና የዳንኩት ባለፈው ነሐሴ ወር ላይ እንጂ በአሁኑ ተይዞ ነበር መባሉን ካደረግኩት ተደጋጋሚ ምርመራ አኳያ ፈፅሞ አልቀበለውም”

“ከጨዋታው በኋላ ያለቀስኩት ከአምና ጀምሮ ስራዬን እንዳልሰራ በጥቂት ደጋፊዎች ምክንያት ቡድኑን የመረበሽ ሙከራ ይደረግብኝ ስለነበርና ያንንም በልጆቼ ቁርጠኝነትና በአመራሮቻችን ድጋፍ ወደ ሻምፒዮንነት ማማው የሚወስደንን ውጤት እያስመዘገብን በመሆኑ ነው”

አሰልጣኝ ስዩም ከበደ /ፋሲል ከነማ/


የፋሲል ከነማው አሰልጣኝ ስዩሞ ከበደ ክለባቸው በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮና ውድድር ላይ ሲዳማ ቡናን በሙጂብ ቃሲም እና በፍፁም አለሙ ሁለት ግቦች 2-1 ካሸነፈ እና መሪነታቸውንም ይበልጥ ካጠናከሩ በኋላ የሀትሪክ ስፖርት ድረ-ገፁ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/
ለአሰልጣኝ ስዩም ከበደ ከጨዋታው በኋላ ሲዳማ ቡናን ስለማሸነፋቸው፣ ከድሉ በኋላ መልበሻ ክፍል ውስጥ ስለማልቀሱ ከባህርዳር ከተማ ጋር ከመጫወታቸው በፊት በኮቪድ ወረርሽኝ ተጠቅቷል ተብሎ ስሙ ስለመነሳቱና ሌሎችም ተያያዥ ጥያቄዎችን አቅርቦለት የሰጠው ምላሽ በሚከተለው መልኩ ቀርቧል።

ከሲዳማ ቡና ስላደረጉት ጨዋታ እና ስላስመዘገቡት ድል

“ከግጥሚያው በፊት ሀይለኛ ዝናብ ዘንቦ ስለነበር የምንጫወትበት ሜዳ ለጨዋታ ምቹ እንደማይሆንና አስቀያሚ እንደሆነም በምናሟሙቅበት ጊዜ በሚገባ ተመልክተን ነበር፤ በምንፈልገው መልኩም ድሪብል እያደረግንም ልንንቀሳቀስ እንደማንችልም ስጋትም ነበረብን። አስቸጋሪ ነገር ይገጥመናል ብለንም ያንንም ነው ልንመለከት የቻልነው። ያም ሆኖ ግን በአጠቃላይ የጨዋታ እንቅስቃሴያችን ላይ ወደ ሻምፒዮንነት ለምናደርገው ጉዞ ከዚህ ግጥሚያ የግድ ሶስት ነጥብን ማግኘት ስላለብን በተጨዋቾቼ ላይ የታየው ቁርጠኝነት ነው ለድል እንድንበቃ ያደረገንና አንዱ ምክንያት ሊሆነን የቻለው። የጨዋታው አሸናፊነታችንን በተመለከተ ከግጥሚያው በኋላ በሁሉም የክለቡ አባላት እና ደጋፊዎቻችን ላይም ነው ከፍተኛ ደስታን ሊፈጥርብን የቻለው”።

በጨዋታው አቻ ከሆኑ በኋላ አንሰራርተው በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች አካባቢ ግጥሚያውን ስለማሸነፋቸው እና ስለ ተጋጣሚያቸው ሲዳማ ቡና

“ሲዳማ ቡና ከእኛ ጋር በነበራቸው ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ አጥቂያቸውን ኢላማ /ታርጌት/ በማድረግና ቀጥተኛ የሆነ /ዳይሬክት/ ፉትቦልን በመጫወት ነው ሲንቀሳቀሱ የነበሩት፤ እንደ እኛ ሙከራን በማድረግ ጭምር ተመጣጣኝ የሆነን እንቅስቃሴንም ነበር ሲያሳዩ የነበሩት። በሁለተኛው አጋማሽ ላይ ደግሞ ጨዋታው እንደተጀመረ ያስቆጠሩት የአቻነት ግብ እነሱን እንዲነሳሱ ቢያደርጋቸውም የእኛ ቡድን ጊዜ ሳይፈጅበት ወደ ጨዋታው ቶሎ ሊገባ በመቻሉና በአጠቃለይ እንቅስቃሴውም ከዚህ ቀደም ከሚታወቅበት የ4-3-2-1 እና የ4-1-4-1 አጨዋወትም በመውጣት ወደ 4-4-2 እንቅስቃሴም የተጨዋቾች ቅያሪ አድርጎ ጭምር በመጫወቱ ያ ሊጠቅመው ችሎ በመጨረሻ ደቂቃዎች አካባቢ ባስቆጠርነው ግብ ከአቻነት አንሰራርተን በመምጣት ጨዋታውን ልናሸነፍ ችለናል”።

የድል ጎሉን ስላስቆጠረው ፍቃዱ አለሙ

“ስለዚህ ተጨዋች የእውነት ብዙ ነገርን ማለት እፈልጋለሁ፤ የድል ጎሉን ማስቆጠሩሞ በጣም እንድደሰትበትም ነው ያደረገኝ። ፍቃዱ ይሄን ቡድን ከተቀላቀለበት ጊዜ አንስቶ ለክለቡ በበቂ ግጥሚያዎች ላይ ተሰልፎ ባይጫወትም ትዕግስተኝነቱ በጣም ይገርማል። የአሰልጣኞችን ውሳኔ ይረዳል፤ ያከብራልም ጭምር፤ በልምምድ ላይ መቶ ፐርሰንት ያለውንሞ ይሰጣል። ለክለቡ እና ለተጨዋቾቹ ያለው ፍቅርም ይገርማል። ያበረታታቸዋል። እነሱም ይወዱታል። የጨዋታ ዲሲፕሊን ማለት ይሄ ነው። የፕሮፌሽናል ተጨዋችነትን ባህሪም በሚገባም ተመልክቼበታለውና ለእሱ ተቀይሮ በመግባት ጎል ማግባቱም ለነገ የራስ መተማመንን ስሜት ይፈጥርለታልና በክለቡ ውስጥ እያደረገ ላለው ነገር ሊመሰገን ይገባዋል”።

ሲዳማ ቡናን ካሸነፉ በኋላ በመልበሻ ክፍል ውስጥ ስለማልቀሱ

“አዎን ያልቀስኩበት ሁኔታ ይሄን ቡድን ከአምና ጀምሮ ሳሰለጥን ብዙ ያየዋቸውና የተረዳዋቸው ደስ የማይሉ ነገሮች በአቅራቢያችን ስለነበሩ ነው። ውስን ደጋፊዎችም ናቸው ስራዬን እንዳልሰራ ምቹነት የማይሰጡኝ የነበሩት። ደጋፊዎቹ ለክለቡ አስበው ያደረጉት ቢሆን ኖሮ ምንም አልልም ነበር። የእነሱ ሀሳብ ግን ይሄ ስራዬን ለማሳጣት የሚያደርጉት ነበርና ሁኔታዎቹ ሲደጋገምብኝና የፋሲል ከነማም ችግር የአሰልጣኙ ነው እያሉ በእኔ ላይ የተለያዩ ጥሩ ያልሆኑ ነገሮችን ያወሩብኝ ስለነበር ጭራሽ ብሎ ደግሞ ከባህርዳር ከተማ ጋር በነበረን ጨዋታ ላይም ስዩም አውት የሚል መፈክርን ይዘው በመግባትም እኔን ከክለቡ እንድሰናበት ስራዬ ላይ መሰናከል ለመሆን እስከመቃወም ደረጃም ላይ ደርሰው ስለነበሩ በተጨዋቾቼ ቁርጠኝነትና ከክለባችን ቦርድ አንስቶ እስከ አመራሮቻችን እንደዚሁም ደግሞ የቡድናችንም መሪ ከጎኔ ስለሆነም ጥሩ ሆነን ጭምር የእኛ ነገር የማይዋጥላቸው ደጋፊዎች ስለነበሩም ነው ያ እልማቸው እንዳይሳካ ስላደረግኩኝና የቡድናችንን የውጤት ማማንም ወደላይ ከፍ አድርገን ስለሰቀልነውም ነው በክለቡ ውስጥ ካሰለፍኩት አጠቃላይ ነገሮች በመነሳት የደስታ ስሜቱ ፈንቅሎኝ ለማልቀስ የቻልኩት። በፋሲል የእዚህ ዘመን የሀላፊነት ቆይታዬ ባለማወቅ ሊሆን ይችላል ይቅርታ የጠየቁኝ ደጋፊዎች አሉ። ይቅርታቸውንም ተቀብዬዋለሁኝ”።

ከፋሲል ከነማ የአሰልጣኝነት ኃላፊነቱ ለመልቀቅ አስቦ ስለመተዉ

“በአንድ ወቅት ለክለቡ በማያስቡ ጥቂት ደጋፊዎች ምክንያት ሪዛይን ለማድረግ ተቃርቤ ነበር። ያም ሆኖ ግን የቡድኑ ቦርድና ማኔጅመንት እንደዚሁም ደግሞ ሁሌም ከጎኔ በመሆን ብዙ ነገሮችን የሚያግዘኝ የቡድን መሪያችን ሀብታሙ ዘዋለ ለሌላ ነገሮች ጆሮዬን ሳልሰጥ ስራዬ ላይ በማተኮር እንድሰራ ከውጪ ለሚመጡብኝ አላስፈላጊ ነገሮች የሚሸከሙልኝ ጥሩ ጥሩ ነገሮች ስለነበሩ ሀሳቤን በመቀየር ከክለቡ ጋር ልቀጥል ችያለሁ”።

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ባህርዳር ከተማን ከመግጠማቸው በፊት በኮቪድ ወረርሽኝ ተጠቅቶ እንደነበር

“ይሄ የአሁኑን በፍፁም አልቀበለውም፤ በኮቪድ ወረርሽኝ እኔ የተጠቃሁት አሁን ሳይሆን ባለፈው ነሐሴ ወር ላይ ነበር። ያኔ ቤቴ እያለው በጣም አሞኝ እያሰቃየኝ ነበር። ራሴን ኳራንቲ አድርጌም ከሰዎች ለ14 ቀን ያህል ርቄና ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ሄጄ በመታከምም ለ17 ቀን ያህል ተኝቼም ነበር። ኳስ ከብዙ ሰዎች ጋር አስተዋውቆኝ ስለነበር እዛ ህክምናዬን አድርጌና ዶክተሮቼና ነርሶቼም እኔን ከማከም ባሻገር በደንብ አድርገው ስለተንከባከቡኝ ጭምርም ከህመሙ ልድን ቻልኩ። ከዛ በኋላም ለሁለት ጊዜ ያህል በራሴ ተመርምሬም ነጋቲቭ ተብዬም ነበር። የአሁኑን በተመለከተ ግን የሚደንቅ ነው። እኔ ምንም አይነት የህመም ስሜት የማይሰማኝ ጤነኛ ሰው ነበርኩ። የጨዋታው ቀን ላይ ግን ስመረመር ፖዘቲቭ ተባልኩ። ከሁለት ቀን በኋላ ስመረመር ደግሞ ነጋቲቭ ተባልኩ። ከሲዳማ ቡና ጋር ለነበረን ጨዋታም ደግሞ እኔን ጨምሮ ኮቺንግ ስታፋችን ተመርምረን ነጋቲቭ ልንባል የቻልንበት ሁኔታም ስላለ ይሄ የምርመራው ሁኔታ በጣም ነው እያስገረመኝ ያለው”።

ስለ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ቀጣይ ጨዋታዎቻቸው

“በተከታታይ ካሉን ሁለት ጨዋታዎች መካከል ከሀድያ ሆሳዕና እና ከአዳማ ከተማ ጋር የምናደርጋቸውን ግጥሚያዎች ማሸነፍ መቻል የእኛን ሻምፒዮንነት እንድናውጅ ያስችለናልና አሁን ካለን ጥሩ ስነ-ልቦና አኳያ ይሄን ድል የምናሳካው ይመስለኛል፤ ሁለቱን ጨዋታ አሸነፍን ማለትም የሐዋሳ ስታዲየም ጨዋታዎቻችን ገና ሳይደረጉ እዚሁ የውድድሩ የበላይነታችንን የምናረጋግጥበትም ሁኔታ ይኖራልና ወደ ሐዋሳ ከተማ ስናመራ ከግብ ጠባቂ አንስቶ ሌሎቹን የመጫወት እድልን ያላገኙ ተጨዋቾችን እንዲሰለፉ በማድረግ የራሳቸውን አቅም እንዲመለከቱበትም ነው የምናደርጋቸው”።

በመጨረሻ

“በፋሲል ከነማ የአሰልጣኝነት ዘመን ቆይታዬ ይህን የሊግ ዋንጫ ለማንሳት ከጫፍ እየደረስን ያለበት ሁኔታ ስላለ የእዚህ ታሪካዊ ድል ትልቁ ባለቤት ለመሆን በመቃረቤ ከፍተኛ ደስታ እየተሰማኝ ይገኛል። ፋሲል ከነማ ባለፉት ሶስት ዓመታቶች ይሄን ዋንጫ ለማንሳት ጠንካራ ቡድንን ፈጥሮ ሁለቱን ዓመታት አንዱን እስከመጨረሻ ሰዓት ድረስ እስከ ፍፃሜ ቀርበን ሌላውን ደግሞ ሊጉን እየመራን ኮቪድ በመግባቱና ጨዋታዎቹ ስለተቋረጡ እነዚህን የስኬት ድሎች ሳናጣጥማቸው ቀርተን ነበር። በዚህ ዓመት ላይ ግን ይህን ድል ለመጎናፀፍ እንድንችል ከጫፍ ደርሰናልና ቡድኑን ከተቀላቀልኩበት ጊዜ ጀምሮ ከእኔ ጋር መልካም እና አሪፍ ግንኙነት ላላቸው እና ው እያሳኩ ላሉት ተጨዋቾቼ፣

Editor at Hatricksport website

Facebook

መሸሻ ወልዴ

Editor at Hatricksport website