“ለወላይታ ዲቻ ጎሎችን ማስቆጠሬ የእኔ ብቻ ሳይሆን የቡድን ጓደኞቼ እገዛ ጭምር ነው” ስንታየሁ መንግስቱ

ትላንትናው ዕለት በተካሄደው የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ላይ ደምቀው ከነበሩት ተጫዋቾች መካከል የጦና ንቦቹ የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች ስንታየሁ መንግስቱ ዋንኛው ተጠቃሽ ሲሆን ድሬዳዋ ላይ ቡድኑ ድሬዳዋ ከተማን 3-1 አሸንፎ ድልን ሲቀዳጅ ሁለት ጎሎችን ከማስቆጠር ባለፈ አንድ ለግብ የሚሆን ኳስም አመቻችቶ በማቀበል አድናቆትን አትርፏል ።

ከሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ ስንታየሁ መንግስቱ ከሀትሪክ ስፖርት ድህረ-ገጽ ፀሀፊው ቅዱስ ዮፍታሔ ጋር ስለ ጨዋታው ፣ ስለ ወደፊት እቅዱ እና የተለያዩ ነጥቦች ላይ ቆይታን አድርጓል።

ድል ስላደረጉበት ጨዋታ

” በመጀመሪያ ፈጣሪ ይመስገን ከሽንፈት መልስ ያገኘነው ውጤት ስለሆነ እንደ ቡድን ደስ ብሎናል፤ ሁለት ጎሎችን በማስቆጠሬ ደስታ ቢሰማኝም ይህ ስኬት የእኔ ብቻ አይደለም የቡድን አጋሮቼ ጭምርም ነው ። ፈጣሪ ይመስገን ከዚ የተሻለ ነገር ከቡድኔ ጋር ለመስራት እየጣርኩም ነው።
ጠንክረን ከሰራን እንደ ቡድን ከዚህ በላይ መሆን እንችላለን፤ ደግሞም ጠንክረን እየሰራን ነው”።

ስለ ወደፊት እቅዱ

“በአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ስር እኔ ብቻ ሳልሆን ብዙዎቻችን በጣም ጥሩ ነገርን እየተማርን ነው፤ እንደ ግልም፣ እንደ ቡድንም ጥሩ እየተጫወትን ነው። እሱ ልምምድን እንደ አባተ እንዲሁም እንደ ወንድም ሆኖም ነዉ የሚያሰራን፤ በእርሱ ሰር እየተሻሻልን ነው፤ ብዙ ነገርም በቀጣይነት እንማራለን ። በቀሪው የውድድር ጊዜያትም ከፈጣሪ ጋር ለቡድኔም ሆነ ለራሴ የተሻለ ነገር ለመሰራትንም አስባለው።

ስለ ጎል አስቆጣሪነቱ

በ 2011 የውድድር ዓመት በ17 ጨዋታ አስራ ስድስት ጎል ነው ያገባሁት፤ በአርባ ምንጭም በነበረኩበት ጊዜ የተሻለ ጎሎችን አስቆጥሬያለው። በወላይታ ድቻ በሚኖረኝ ቆይታም ከዚህ በላይ ጎሎችን ማግባትም ነው የምፈለገው። ጥሩ ነገር እሰራለው ብዬም አሰባለሁ ” ሲል የጦና ንቦቹ የፊት መስመር አጥቂ ስንታየሁ መንግስቱ አስተያየቱን ሰጥቶናል።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor