ድሬዳዋ ጤና ቢሮ ከ ሃሮማያ ዩኒቨርስቲ

11 ተጨዋቾች በሙሉ ኮቪድ 19 አለባቸው”
ድሬዳዋ ጤና ቢሮ

“ከ11ዱ ኮቪዱ የተገኘባቸው 3ቱ ብቻ ናቸው”
ሃሮማያ ዩኒቨርስቲ

ነገሩ ሲታይ ግጥሚያ ይመስላል ሁሉቱም አይተማመኑም እልህ ተያይዘዋል…ጤና ቢሮው 27 ተጨዋቾች በኮቪድ 19 ተይዘዋል ብሎ ሃሮማያ 4ቱ ናቸው 23ቱ ነጻ ናቸው ሲል ትላንት ደግሞ ኢትዮጵያ ቡናና ሀዋሳ ተመሳሳይ እጣ ገጥሟቸዋል።

ድሬዳዋ ጤና ቢሮ 15 የሀዋሳ ከተማ 13 የኢትዮጵያ ቡና ተጨዋቾች ኮቪድ 19 ተገኝቶባቸዋል ቢልም ሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ግን ከሀዋሳ 3 ከኢትዮጵያ ቡና ግን 2 ተጨዋቾች ብቻ ኮቪድ እንደተገኘባቸው መነገሩ ለድሬዳዋ 4 ሰው ለሀረር 1 ሰው ማለት ይሆን የሚል ጥያቄ አስነስቷል።
ይህ የሁለቱ ተቋማት ውዝግብ አስቸግሮ ዛሬ ጠዋት በድሬዳዋ ጤና ቢሮ ኮቪድ አለባቸው የተባሉ አንድ አንድ ተጨዋቾች ላኩ ተብሎ ለ13 ክለቦች ጥያቄ ቀርቦ ከ11ንዱ ክለቦች 11 ተጨዋቾች የተመረመሩ መሆኑ ታውቋል።

ሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ደግሞ ከ 11ዱ 3ቱ ላይ ብቻ ነው ቫይረሱ የተገኘው ብሏል… ያም ሆኖ የድሬዳዋ ጤና ቢሮ ግን ከሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ለምን ውጤት ትቀበላላችሁ የሚል ቅሬታ አቅርቦ “ከተፈቀደላቸው ህጋዊ ተቋማት የተላክ ህጋዊ ውጤት አንቀበልም የምንልበት ምክንያት የለንም የኛም ስልጣን አይደለም” ብሎ ሊግ ካምፓኒው የሰጠው ምላሽ ድሬዳዋዎችን ቅሬታ ውስጥ ከቷል።

ሊግ ካምፓኒው የሁለቱን ተቋማት ውጤቶችን ወደ ህብረተሰብ ሳይንስ ኢንስቲትዩት በመላክ ምርመራ መጀመሩና የቱ ነው ትክክል የሚለው እየተጣራ መሆኑ ታውቋል። ከህብረተሰብ ጤና ሳይንስ ደግሞ የድሬዳዋን መመርመሪያ ማሽንን ለማየትና ችግሩን ለማወቅ ባለሙያዎች ወደ ድሬዳዋ መላካቸው ታውቋል።

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport