አሰልጣኝ ስዮም ከበደ በዛሬው ጨዋታ ቡድናቸውን አይመሩም!

ከደቂቃዎች በኋላ በሚጀምረው ተጣባቂው የዚህ ሳምንት መርሐ ግብር አፄዎቹ ያለ ዋና አሰልጣኛቸው ስዩም ከበደ ጨዋታቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል ።

በምትኩም የፋሲል ከተማ የቡድን መሪ ሀብታሙ ዘዋለ የዛሬውን ተጠባቂ ጨዋታ በጊዜያዊ አሰልጣኝነት የሚመሩ ይሆናል ።

ሀብታሙ ዘዋለ ከጨዋታ በፊት በሰጡት አስተያየት እንዳሳወቁት አሰልጣኝ ስዩም ከበደ የመጨረሻ ልምምድ ካሰሩ በኋላ መጠነኛ ህምም የተሰማቸው መሆኑን ተከትሎ የዛሬውን ጨዋታ እንደማይመሩ ገልፀዋል ።

ሀትሪክ ስፖርት ከ ስፍራው ለማወቅ እንደቻለችው ከሆነ አሰልጣኙ በ ኮቪድ መያዛቸው ለማወቅ ሲቻል ከጨዋታው ጅማሮ በፊት በስታዲየም መገኘታቸው አነጋገሪ ቢሆንም ወደ ክለቡ ሆቴል በአሁን ሰዓት መመለሳቸውን ለማወቅ ችለናል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor