ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ 18ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

በአስራ ስምንተኛ ሳምንት የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች አስራ ሁለት ጎሎች ከመረብ ላይ ሲያርፉ የኢትዮጵያ ቡናው አቡበከር ናስር እና የወላይታ ድቻው ስንታየሁ መንግስቱ በሳምንቱ ሁለት ጎሎችን ማስቆጠር የቻሉ ብቸኞቹ ተጫዋቾች ናቸው ።

በአስራ ስምንተኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች ሀያ አንድ የማስጠንቀቂያ ቢጫ ካርዶች ሲመዘዙ የወልቂጤ ከተማው ቶማስ ስምረቱ እና የፋሲል ከተማው አለም ብርሀን ይግዛው በቀይ ካርድ ከሜዳ የወጡ ተጫዋቾች ናቸው ።

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች :-

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ቅዳሜ ሚያዚያ 6/2013 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች) ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የሚከተሉትን የዲሲፒሊን ዉሳኔዎች አስተላፏል፡፡

1. የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ተጫዋች የሆነው ቶማሰ ስምረቱ ከ ሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ጋር ባደረገው የ18ኛ ሳምንት ጨዋታ በ 52ኛ ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያሰጥ ጥፋት በመፈፀሙ ቀይ ካርድ አይቶ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል።

ቶማስ ስምረቱ ለፈፀመው ጥፋት ለአንድ ጨዋታ እንዲታገድ ተወስኗል።

2. የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ተጫዋች የሆነው አለምብርሀን ይግዛው ከ ባህርዳር ከተማ እግር ኳስ ክለብ ጋር ባደረገው የ18ኛ ሳምንት ጨዋታ ላይ ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ በመጫወቻ ሜዳ ውስጥ እያለ ዳኛን አፀያፊ ስድብ በመሳደቡ ቀይ ካርድ መመልከቱን ከ ዳኛው እና ከ ኮሚሽነሩ ሪፖርት ቀርቦበታል።

ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት መሰረት ሶስት ጨዋታ እንዲታገድ እና 3000.00 /ሶስት ሺህ/ ብር እንዲከፍል ተወስኖበታል፡፡

3. አዳማ ከነማ ከ ሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ጋር ባደረገው ጨዋታ ላይ በ 31ኛው ደቂቃ ላይ የተቆጠረችው ግብ ከጨዋታ ውጭ ነች ትክክል አይደለችም በማለት የቴክኒክ ክስ አስይዘዋል።

በመሆኑም የውድድር አመራር እና ስነ-ስርአት ኮሚቴ የዳኛውን እና የኮሚሽነርን ሪፓርት መነሻ በማድረግ የጨዋታውን ቪድዮ በመመልከት ግቧ ትክክለኛ ግብ መሆኗን አረጋግጧል።

በመሆኑም ለክስ መመስረቻ ያስያዙት 1000.00 /አንድ ሺህ/ ብር ለሊግ ካምፓኒው ገቢ እንዲሆን ተወስኗል።

ማሳሳቢያ

1. በ17ኛ ሳምንትና በ18ኛ ሳምንት ውድድር ላይ ወደ ስቴዲየም እንዲገቡ ፍቃድ የተሰጣቸው የክለብ የቦርድ አባላት በውድድር ሜዳ ላይ አላስፈላጊ እና ስፓርታዊ ያልሆኑ ባህሪያቶችን ሲያሳዩ እንደነበር አወዳዳሪው አካል ታዝቧል። ስለሆነም በቀጣይ በቦርድ አባላት ስም የሚገቡ አካላት ቋሚ የሆነ የስማቸው ዝርዝር ቀደም ብሎ በክለቡ ማህተም በማስደገፍ ከውድድሩ ቀን በፊት ለአወዳዳሪው አካል እንዲደርስ እንድታደርጉና የሚገቡትም በስፓርታዊ ጨዋነት ብቻ ውድድሩን እንዲመለከቱ እያልን ይህን በማያደርጉትና አላስፈላጊ ባህሪያት በሚያሳዩ የክለብ ቦርድ አመራሮች ላይ አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ ለመዉሰድ የምንገደድ መሆኑን እናሳውቃለን።

2. በኮቪድ-19 የተያዙ ተጨዋቾች እና የቡድን አመራሮች በተለያዩ ወቅት በ ከተማ ውስጥ እና በስታድየም አካባቢ ከክለቡ ጋር እንቅሳቃሴ ሲያደርጉ እየተስተዋለ ነው።

በቀጣይ በቫይረሱ የሚያዙ የቡድን አባላት በኮቪድ-19 ፕሮቶኮሉ መሰረት ራሳቸውን አግለው ከቡድኑ ጋር ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ እና ከመወዳደሪያ ስፍራዎች ራሳቸውን አርቀው ከህመሙ እስኪያገግሙ ድረስ በማረፊያቸው ብቻ እንዲቆዩ እያሳሰብን ይህ ሳይሆን ቢቀር የፀጥታ አካላት ለሚወስዱት እርምጃ ሀላፊነቱ የግለሰቡ እና የክለቡ መሆኑም እናሳውቃለን።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor