ወላይታ ድቻ ስሙ ሲነሳ በጠንካራ የኮሪደር ስፍራ ተጨዋችነታቸው ከሚጠቀሱት ተጨዋቾች መካከል አንዱ የሆነውና ባሳለፍነው የውድድር ዘመን የከፍተኛ ሊግ ተወዳዳሪ ለነበረው መከላከያ ተጫውቶ ያሳለፈው አናጋው ባድግ በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ የአንደኛው ዙር የፍፃሜ ጨዋታ ሲዳማ ቡናን በራሱ ብቸኛ ግብ 1-0 ያሸነፈ ሲሆን ባስቆጠራት የድል ግብም ዙሪያ “አስቤያት ያስቆጠርኳት ግብ አይደለችም፤ ለመከላከል ብዬ ከራሳችን የግብ ክልል ለማራቅ የመታዋት ኳስ ነው”ጎሉን አጋጣሚ ለመከላከል ነበር ያሰብኩት ሆኖም ግን ወደ ግብነት ተቀይሯል በማለት አስተያየትን ሰጥቷል”።
የጦና ንቦቹን በዛሬው ዕለት አሸናፊ ያደረገችውን ግብ ማስቆጠር የቻለው እና የጨዋታው ኮከብ በመባል የተመረጠው አናጋው ባደግ ከሀትሪክ ስፖርት ፀሀፊ ቅዱስ ዮፍታሔ ጋር ቆይታን አድርጓል ።
ስለ ዛሬው ጨዋታ . . . . . .
- ማሰታውቂያ -
ጨዋታው እንደተመለከታችሁት ነው በተመሳሳይ ነጥብ እንደመገኘታችን የግድ አንደኛውን ዙር የመጨረሻ ጨዋታ አሸንፈን
ካለንበት ደረጃ ከፍ ብለን እንጨርሳለን ብለን አስበን እና ተነጋግረን ወደ ሜዳ የገባነው ያንንም አሳክተን ወጥተናል ።
አሸናፊ ሳላደረገቻቸው ግብ . . . . .
ጎሉን አጋጣሚ ለመከላከል ነበር ያሰብኩት ሆኖም ግን ወደ ግብነት ተቀይሯል ፣ በዚህም በጣም ደስ ብሎኛል ።
ስለ ወቅታዊ አቋም እና ስለ አምበሉ ደጉ ደበበ . . . . . .
በሁለተኛው ዙር በእርግጠኝነት ለወራጅነት አንጫወትም ፣ ደረጃ ውስጥ በመግባት በጥሩ ውጤት የውድድር ዓመቱን ለመጨረስ እየተዘጋጀን ነው ።
ከደጉ ጋር አብሬው በመጫወቴ በጣም ዕድለኛ ነኝ ፣ ሲቀጥል ያለውን እና ያካበተውን ልምድ እያጋራን በጥሩ ሁኔታ እገዛን ያደርግልናል ። አዲሱ አሰልጣኛችንም ዘላለም ሽፈራውም ቢሆን በጥሩ ሁኔታ ቡድኑን እየቀየረው ሲገኝ ወደፊትም ከዚህ የበለጠ የተሻለ ነገር እንደሚሰራ እምነቱ አለኝ ።
አብሮ መጫወት ስለሚያልመው ተጫዋች . . . . . .
በፕርሚየር ሊጉ አብሬው ብጫወት ብዬ ከማስባቸው የኋላ መስመር ተጫዋቾች ውስጥ ቀዳሚው የቅዱስ ጊዮርጊሱ አስቻለው ታመነ ነው ። አስቻለው ታመነን በጣም ነው የምወደው ከእርሱ ጋር የመጫወት እድልን ባገኝ በጣም ደስ ይለኛል ።