በቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ደካማ ጅማሮን እያደረጉ የሚገኙት ሲዳማ ቡናዎች በ አዲሱ አሰልጣኛቸው ገብረ መድህን ሀይሌ እየተመሩ አራት ተጫዋቾችን ለማስፈረም መስማማታቸው ተገልጿል ።
ሀትሪክ ስፖርት ባገኘችው መረጃ መሰረት በጅማ አባ ጅፋር የሊጉን ዋንጫ ማሳካት የቻለው አጥቂው ኦኪኪ ኦፎላቢ ከ ናይጄርያ በዛሬው ዕለት በመመለስ ይፋዊ ስምምነት የሚፈርም ይሆናል ።
አሰልጣኝ ገብረ መድህን ሀይሌ ከ ኦኪኪ በተጨማሪም በመቐለ 70 እንደርታ የሚያቁትን ዮናስ ገረመውን ጨምሮ መሀሪ መና እና ሽመልስ ተገኝን ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል ።
በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት ባሳለፉት ዓመታት የሚታወቀው መሀሪ መና ፣ ዮናስ ገረመው እና ሽመልስ ተገኝ በዛሬው ዕለት ከቡድኑ ጋር በስታዲየም በመገኘት ጨዋታውን እየተከታተሉ ይገኛል ።
የዘንድሮው የውድድር ዓመት የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ከነገው ዕለት ጀምሮ በይፋ የሚከፈት ይሆናል ።
አስተያየት ይስጡ