የከፍተኛ ሊግ የ2014 ዓ.ም ውድድር የዕጣ ማውጣት ስነ ሥርዓት ተካሄደ።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን  ስር የሚመራው የከፍተኛ ሊግ ውድድር የ2014 ዓ.ም የዕጣ ማውጣት ስነ ሥርዓት እና የውድድር ደንብ ማጽደቅ ዛሬ ህዳር 15/2014 ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ  ካሳንቺስ በሚገኘው ጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል ተካሂዷል ።

በዕለቱ አቶ አሊሚራህ ሙሐመድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና የከፍተኛ ሊግ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፣  አቶ ሰለሞን ገ/ ሥላሴ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ም/ዋና ፀሐፊ አቶ ቴዎድሮስ ፍራንኮ የቴክኒክና ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እና አቶ ከበደ ወርቁ የውድድር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እንዲሁ የከፍተኛ ሊግ ኮሚቴ አባላት፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የቋሚ ኮሚቴዎችና የከፍተኛ ሊግ ተሳታፊ ክለብ ተወካዮች፣ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶችና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ተገኝተዋል ።

ኘሮግራሙ ከዚህ ዓለም በሞት ለተለዩ የእግር ኳሱ ባለሙያዎች የህሊና ፀሎት በማድረግ ተጀምሯል።

በመክፈቻው አቶ አሊሚራህ ሙሐመድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና የከፍተኛ ሊግ ኮሚቴ ሰብሳቢ በአደረጉት ንግግር  “በአሁኑ ሰዓት ሀገራችን ኢትዮጵያ የገጠማትን ችግር ለመፍታት በሚደረገው ጥረት  የፌዴሬሽናችን ሠራተኞች ለመከላከያ ሠራዊት የአንድ ወር ደሞዛቸውንና የደም ልገሳ ድጋፍ ለማድረግ ቃል በመግባታቸው ላመሰግናቸው እወዳለሁ ። የከፍተኛ ሊግ ክለቦችም  ከውድድሩ ባሻገር በድጋፉ የበኩላችሁን አስተዋጽዎ በማድረግ ከመከላከያ ሠራዊት ጎን መሆናችሁን  ማረጋገጥ እንዳለባችሁ ላሳስብ እፈልጋለሁ ።” በማለት ለቤቱ በአቀረቡት ሃሳብ ላይ አባላቱ ሀሳቡን በመደገፍ ተወያይቶበት ውሳኔያቸውን ከቀናት በኃላ በፌዴሬሽኑ በኩል እንደሚያሳውቁ ገልፀዋል።

በማሰከተል በሦስት ምድብ ተከፍሎ በሦስት ክልሎች የተካሄደው የ2013 ዓ.ም ውድድር አፈፃፀም፣ የዳኞች ፣ የዲስኘሊን እና የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴዎች ሪፖርት እንዲሁም የ2014 የውድድር ደንብ ቀርበው ከተሳታፊዎች በተነሱ ጥያቄዎች ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ የውድድር ደንቡን አፅድቀዋል።

እንዲሁም የከፍተኛ ሊግ ውድድርን በሚገባ ለማስተዋውቅና የስፖንሰር ሽኘ ገቢ ለማግኘትና የሊጉን የፋይናንሰ አቅም ለማሳደግ እንዲረዳ ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀው የከፍተኛ ሊግ የውድድር  ሎጎ (ዓርማ) ለተሳታፊ ክለቦች ቀርቦ ሀሳቡን በመደገፍ የማዳበሪያ ሃሳቦች የተሰጡበት ሲሆን ተጨማሪ ሀሳቦችን በቀጣይ ቀናት በፌዴሬሽንኑ በኩል እንዲልኩና ማሻሻያ ተደርጎበት በስራ አስፈፃሚ እንደሚፀድቅ ተገልጿል።

በመጨረሻም ለ2014 የውድድር ዘመን ተሳታፊ የሚሆኑ ክለቦች የውድድር እና የመወዳደሪያ ሜዳዎች የዕጣ ማውጣት ኘሮግራም ተገቢውን ክፍያ በወቅቱ በፈፀሙ 23 ክለብ ተወካዮች ተከናውኗል ።

ድልድሉ በሦስት ምድብ የተደለደለ ሲሆን ፣
በምድብ “ሀ”
*******
1. ገላን ከተማ
2. አምቦ ከተማ
3. ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ
4. ሻሸመኔ ከተማ
5. ሀላባ ከተማ
6. ጌዲዮ ዲላ
7. ባቱ ከተማ
8. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ጨዋታ ሜዳ ሀድያ ሆሳዕና ሜዳ

በምድብ “ለ”
******
1. ሲልጤ ወራቤ
2. ለገጣፎ ከተማ
3. ቡታጅራ ከተማ
4. ከፋ ቡና
5. ቤንች ማጂ
6. ቡራዩ ከተማ
7. ቂርቆስ ክ/ከተማ
8. ሰንዳፋ ከተማ
የጨዋታ ሜዳ ሐዋሳ ሜዳ ።  

በምድብ “ሐ”
*******
1. ሀምበርቾ
2. ፌዴራል ፖሊስ
3.  የኢትዮጵያ መድን
4. ነቀምት ከተማ
5. ጉለሌ ክ/ከተማ
6. የካ ክ/ከተማ
7. ደቡብ ፖሊስ

ጨዋታ ሜዳ ጅማ ሜዳ እንደሚስተናገዱ. እና የውድድር ኘሮግራም በደብዳቤ እንደሚገለጽ የውድድር ዳይሬክተሩ አቶ ከበደ ወርቁ ገልፀዋል ።

©EFF

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *