By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: “ተጨዋቾቼ ሜዳውና አየሩን ሲለምዱትና የተጎዱት ሲመለሱ ወደ ውጤታማነት እንመለሳለን” ሙሉጌታ ምህረት /ሀዋሳ ከተማ/
Share
Notification Show More
Latest News
በጨምበላላ ዋዜማ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ጣፋጭ ድል ቀምሷል
ዜናዎች የጨዋታ ዘገባ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
ዩጋንዳዊው የሲዳማ ቡና ግብ ጠባቂ በዛሬው ጨዋታ አይሰለፍም
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች ሲዳማ ቡና
የቅዱስ ጊዮርጊስ የቦርድ አመራሮች ከሀላፊነት ለመነሳት ፍቃደኛ ሆኑ
ዜናዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ
የሲዳማ ቡናው ግብ ጠባቂ ታገደ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች ሲዳማ ቡና
መቐለ 70 እንደርታ ናይጄሪያዊ አጥቂ አስፈረመ
መቐለ 70 እንደርታ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎችሀዋሳ ከተማ

“ተጨዋቾቼ ሜዳውና አየሩን ሲለምዱትና የተጎዱት ሲመለሱ ወደ ውጤታማነት እንመለሳለን” ሙሉጌታ ምህረት /ሀዋሳ ከተማ/

ዮሴፍ ከፈለኝ
ዮሴፍ ከፈለኝ 5 years ago
Share
SHARE

በዮሴፍ ከፈለኝ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን በማንሳት ከክልል ክለቦች ቀዳሚው ነው ጠንካራ ተፎካካሪ በመሆንም ይታወቃል… ሀዋሳ ከተማ፡፡ የ2013 የሊጉ መርሃ ግብር ላይ 2 ጨዋታዎች ተረትቶ ያለምንም ነጥብ ከታች የሚገኘው ሀዋሳ ከተማ ከ13 ክለቦች ሶስቱ በሚወርዱበት ሂደት ወራጅ ይሆን እንዴ የሚለው ስጋት የብዙዎች ቢሆንም ከሀትሪኩ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር ቆይታ ያደርገው የክለቡ ዋና አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት ግን የመውረድ ስጋት በፍፁም የለብንም ሲል መልሷል፡፡ አሰልጣኝ ሙሉጌታ ከሀትሪክ ለቀረቡለት ጥያቄዎችም የሰጠው ምላሽ ይህን ይመስላል፡፡

ሀትሪክ፡- ከቀድሞው የዋሊያዎቹ አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ ጋር የነበረህን ቆይታ እንዴት ታየዋለህ?

ሙሉጌታ፡- ከአሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ ጋር የሰራሁበት ጊዜ ለኔ ምርጡ ጊዜ ነበር፡፡ ከጠበኩት በላይ የተደሰትኩበትም ጊዜ ነው፤ ሀዋሳ ከተማ እያለሁም ከአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጋር ሠርቻለሁ የተሻለ እውቀትና ትምህርት አግኝቼ ነው ሀዋሳ ከተማን የተረከብከት…. በተለይ ከአሠልጣኝ አብርሃም ጋር የነበረኝ ጊዜ ለኔ በራስ መተማመኔን ጨምሮልኛል፡፡

- ማሰታውቂያ -

ሀትሪክ፡- ሀዋሳ ከተማን በተጨዋችነትም በአሰልጣኝነትም ማገልገል ምን ስሜት ይፈጥራል?

ሙሉጌታ፡- ተጫውቼ ያሳለፈኩበትን ክለብን ማሰልጠን ትልቅ ደስታ ይፈጥራል አጋጣሚው መፍጠኑ ደግሞ የተለየ ያደርገዋል የተወለድኩበት ከተማና ያደኩበት ክለብ መሆኑ ያስደስታል… እንደመጀመሪያ ከሌላ ክለብ ይልቅ በሀዋሳ መጀመሬ ለኔ ትልቅ እድል ነው፡፡

ሀትሪክ፡-በሊጉ ጅማሬ 2 ጨዋታ በተከታታይ የመሸነፋችሁ ምክንያት ምን ይሆን?

ሙሉጌታ፡- ምንም የተለየ ነገር የለውም የዘንድሮ የፕሪማየር ሊግ ውድድር ትንሽ ጠንከር ያለ ይመስላል ቡድናችን ውስጥ በርከት ያሉ ወጣቶች እንደመኖራቸው ከተወሰኑ ሲኒየር ተጨዋቾች ጋር አቀናጅተን ወደ ውድድር ብንገባም ዘግየት ማለታችን አስቸግሮናል፡፡ አየሩና የተዘጋጀንበት ሜዳ ሊስተካከልልን አልቻለም የጥቂት ተጨዋቾች ጉዳት ወጥ የሆነ አቋም እንዳናሳይ አድርጎናል፡፡ የአዲስ አበባ አየርና ሜዳው ውጤት ላይ ተፈታትኖናል፡፡ ከጨዋታ ጨዋታ ግን ተከተካክለን የተሻለ አቋም እናሳያለን ብዬ አስባለው፡፡

ሀትሪክ፡-በወጣቶች የተሞላ ቡድን መሆኑ ጥሩ ነው ነገር ግን ፊት ላይ የአጨራረስ ድክመት የሚታይ ይመስላል ይህን ታዝበሃል?

ሙሉጌታ፡-ትክክል ነው ይህ ክፍተት ታይቶብናል፡፡ ተጨዋቾቼ ሜዳውና አየሩን ሲለምዱትና የተጎዱት ሲመለሱ ወደ ውጤታማነት እንመለሳለን ብዬ አምናለሁ አንድ ልምድ ያለው አጥቂንም ብናገኝ ጥሩ ነበር፤ አልተሳካልንም እስራኤል እሸቱ የተሰኘው አጥቂ እኛ ጋር ፈርሞ ቆየና ባለቀ ሰዓት ወደ ሌላ ክለብ ማምራቱ ጎድቶናል ቀድመን ብናውቅ የተሻለ አጥቂ እናስፈርም ነበር.. ነገር ግን ተጨዋቹ የለቀቀው ባለቀ ሰዓት በመሆኑ አልተሳካልንም ያም ቢሆን አሁን ባሉት ወጣቶች ክፍተቶችን እያጠጋገንን 1ኛ ዙርን ለመጨረስ እንሞክራለን፡፡

ሀትሪክ፡-አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት ስራውን የሚሰራው በጫና? ወይስ ዘና ብሎ?

ሙሉጌታ፡-/ሳቅ/ ኧረ ዘና ብሎ ነው ገና ውድድሩ ሳይጀመር የምን ጫና ይኖራል?

ሀትሪክ፡- ከግጥሚያው ጀርባ ያለ ፍትጊያ የለም እያልክ ነው? ቦታውን የሚፈልጉ ሰዎች ጫና ውስጥ ከተውሃል ይባላል ስህተት ነው?

ሙሉጌታ፡-ይህን አላውቅም ነገር ግን ስራ ስትሰራ የሚወድህም የሚጠላህም ይኖራል ይህን አይነት ቻሌንጅ ዛሬ ብቻ ሳይሆን ስጫወትም የነበረ ነው ግን እነዚህ ነገሮች ቢፈጠሩ በሚል ራሴን አዘጋጅቼ ነው የመጣሁት ከሜዳ ውጪ ያለውን ጫና ካልተቋቋምክ ደግሞ ማሰልጠን ይከብዳል ምናልባት ሽንፈት ሲመጣ ጫናው ሊመጣ ይችላልና ነገር ግን በቡድኑ እምነት ስላለኝ የተሻለ ቦታ ላይ እንቀመጣለን ብዬ አስባለሁ፡፡

ሀትሪክ፡-ሀዋሳ ካፈራቻቸው ባለሙያዎች ተጫውተው ባቆሙ ድጋፍ ይደረግልሃል?

ሙሉጌታ፡- /ሳቅ/ በህብረተሰቡ ደረጃ ሙሉ ድጋፍ አለኝ የቡድኑ አሰልጣኞች ተጫውተን ያለፍን እንደመሆናችን በርቱ የሚለን ህዝብ ብዙ ነው ነገር ግን እንደባለሙያ ግን ብዙም አይደለም ባለሙያ የምትላቸውም እኛጋር ብዙም አይደሉም፤ ከጥቂቶቹ መሀል እነ ጋሽ ከማል እነ ዘላለም ሽፈራው /ሞውሪንሆ/ ከነሱ ጋር መገናኘቱ ጠባብ በመሆኑ ተገናኝተን አውርተን አናውቅም፤ ተጫውተው ካቆሙ መሃል የሚቀርቡኝ አሉ ጥሩ ምላሽም አላቸው ነገር ግን ሌሎች ችግሮች ካሉ አላውቅም እገዛው ግን ባለህ ግንኙነት የሚወሰን ይመስለኛል ሁሌ በእኔ በኩል ትኩረቴ ስራ ላይ ብቻ መሆኑን ነው የማውቀው፡፡

ሀትሪክ፡- በደመወዝና ማበረታቻ መዘግየትስ የተፈጠረ ችግር የለም?

ሙሉጌታ፡- በርግጥ ስፖርትኛ ላይ ትልቅ ተፅዕኖ የሚፈጥረው ይሄ ነው ከኛ ጊዜም ጀምሮ ቡድኖችን የሚጎዳ ነገር ከተባለ ከጥቅማ ጥቅምና ደመወዝ ጋር የተያያዘ ግጭት ነው የኛ ክለብ ግን በክፍያ አይታማም በተለይ ደግሞ ደመወዝ በጊዜ በመክፈልና ማበረታቻ በመስጠት አይታማም የተፈጠረ ክፍተትም የለም ጥሩ አካሄድ ላይ እንገኛለን፡፡

ሀትሪክ፡- ከ13 ክለቦች 3ቱ ይወርዳሉ ፉክክሩ ከባድ እንደመሆኑ አያሰጋችሁም?

ሙሉጌታ፡-በርግጥ የዘንድር የሊግ ውድድር ከብዷል ሶስት ክለቦች ወራጅ መሆናቸው በራሱ ይከብዳል እኛን ግን የሚያሳስበን ነገር ያለ አይመስለኝም፤ ጠንካራ ስምና ጠንካራ ቡድን ያለው ክለብ እንደመሆኑ አሁን የታየው ሽንፈት ከ3 እና 4 ጨዋታዎች በኋላ አይኖርም ራሳችንን ፈትሸን ሊጉ ላይ ጠንክረን እንደምንገኝ ርግጠኛ ነኝ… ወጥ የሆነ አቋማችንን ማሳየታችን አይቀርም፡፡

ሀትሪክ፡- የ2013 የአሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረትና ቡድኑ ግብ ምንድነው?

ሙሉጌታ፡- ያለን ግብ ቡድናችን በየደረጃው እየተጓዝን ጠንካራ ቡድን የመገንባት እቅድ አለን፡፡ ክለባችን የሊጉን ዋንጫ በማንሣት ይታወቃል፡፡ ደረጃ ውስጥ የማይጠፋ ክለብ ነው አሁን ደግሞ ጠንካራ ቡድን እየገነባን ከጊዜያት በኋላ የዋንጫ ተፎካካሪና ደረጃ ውሰጥ የሚቆይ ቡድን ለመፍጠር አቅደናል፡፡

ሀትሪክ፡- የመጨረሻ ጥያቄ… በ2013 የሀዋሳ ከተማ ቡድን የመውረድ ስጋት የለበትም ማለት ይቻላል?

ሙሉጌታ፡- በፍፁም የመውረድ ስጋት የለብንም በውስጣችን ርግጠኞች ጠንካራውን ሀዋሳ ከተማ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ይታያል እንጂ የመውረድ ስጋት በፍፁም አይታሰብም…፡፡

You Might Also Like

በጨምበላላ ዋዜማ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ጣፋጭ ድል ቀምሷል

ዩጋንዳዊው የሲዳማ ቡና ግብ ጠባቂ በዛሬው ጨዋታ አይሰለፍም

የቅዱስ ጊዮርጊስ የቦርድ አመራሮች ከሀላፊነት ለመነሳት ፍቃደኛ ሆኑ

የሲዳማ ቡናው ግብ ጠባቂ ታገደ

መቐለ 70 እንደርታ ናይጄሪያዊ አጥቂ አስፈረመ

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By ዮሴፍ ከፈለኝ
Follow:
Editor at Hatricksport
Previous Article ሀብታሙ ታደሰ የኢትዮጵያ ቡና የውጤታማነት ምስጢር
Next Article “የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ እንዳናነሳ ያደርገናል ብዬ የምሰጋው አንድም ክለብ አላየሁም” አብዱልከሪም መሐመድ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎችCovid-19

አስር የእግርኳሱ ባለውለተኞች ድጋፍ ተደረገላቸው

ዮሴፍ ከፈለኝ By ዮሴፍ ከፈለኝ 6 years ago
ወልቂጤ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና | ቀጥታ የውጤት መግለጫ
ቅድመ ዳሰሳ | ኢትዮጵያ ቡና ከ ወላይታ ድቻ እና መከላከያ ከ ፋሲል ከተማ
ጌዲኦ ዲላዎች የአምስት ነባር ተጨዋቾቹ ውል ሲያራዝሙ ሥስት ተጨዋቾችን አስፈርመዋል
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 3ኛ ሳምንት 6ጨዋታዎች ዛሬ ተደርገዋል።
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
Welcome Back!

Sign in to your account

Lost your password?