“አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ እንዲሁ እንደ ቀልድ ጥሎን ይሄዳል ብለን አንሰጋም ” አቶ መላኩ ማዶሮ / የሀዲያ ሆሳዕና እግርኳስ ክለብ ዋና ስራ አስኪያጅ/

 

.አቶ መላኩ እንደተናገሩት” ከአሰልጣኝ አሸናፊ ጋር ተነጋግረናል በፍጹም ውሸት ነው አይደረግም ብሎናል አሰልጣኝ አሸናፊ እንደቀልድ ጥሎን ይሄዳል ብለን አናምንም በኛ በኩል ቃል የገባነውን ገንዘብ አካውንቱ ውስጥ ገብቷል ሰበታዎችም የኛን ክለብ አፍርሰው የመሄድ ፕላን አላቸው ብዬ አላምንም ዜናውን አንድ ኤጀንት ነው ለራሱ ቢዝነስ ሲል ያወራው ለተጨዋቾች ቃል የገባነው መስከረም 25 እንደሚከፈላቸው ነው ቃላችንን ጠብቀናል በዚህ በኩል ምንም ስጋት የለንም” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

 

አቶ መላኩ “በረከት ሲጀመር ለኛ የፈረመው በአሰልጣኙ ማግባባት ነበር ብዙም ፍላጎት አልነበረውም ቃል የገባንበት መስከረም 25 ከመድረሱ በፊት ወደ ፋሲል ከነማ ዝውውር በማድረጉ ምንም ማድረግ አልተቻለም አበበም ለቡና ቢፈርምም በቦታው ዑጋንዳዊ ተጨዋች አዘጋጅተን ስለሆነ የሁለቱም አይጎዳንም” በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport