ቡናማዎቹ ተጫዋች አስፈርመዋል !

በአሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ የሚመሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች ለአርባ ምንጭ ፣ ሲዳማ ቡና እና መከላከያ በመጫወት ያሳለፈውን የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች አበበ ጥላሁንን ማስፈረማቸውን አሳውቀዋል ።

አበበ ጥላሁን በዛሬው ዕለት ከቡናማዎቹ ጋር የሚያቆየውን የአራት ዓመት ኮንትራት በክለቡ ፅ/ቤት በመገኘት ፊርማውን አኑሯል።

በተያያዘ መረጃ ለኢትዮጵያ ቡና ለመጫወት ውላቸውን ያደሱ እና ውላቸውን ያራዘሙ ተጫዋቾች በሙሉ (ብሔራዊ ቡድን ዝግጅት ላይ ያሉትንም ጨምሮ) ፌዴሬሽን በመቅረብ የውል ስምምነታቸውን ማረጋገጣቸውን የክለቡ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ አስነብቧል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor