ፋሲል ከነማ በሙጂብ ቃሲም
ዝውውር ዙሪያ ስምምነት ላይ አልደረስንም አለ
,…ተጨዋቹና የአልጄሪያው ክለብ ግን
ተስማምተዋል
የፋሲል ከነማው አጥቂ ሙጂብ ቃሲም ወደ አልጄሪያው ክለብ ጂ ኤስ ካባሊ የሚያደርገው ዝውውር መቋጫ እንዳልተበጀለት ክለቡ አስታውቋል።
ሙጂብ ከፋሲል ከነማ ጋር ቀሪ የአንድ አመት ውል ያለው ሲሆን የተገኘው እድል ከክለብም አልፎ ለሀገር ትልቅ ትርፍ ያለው በመሆኑ ዝውውሩ የክለቡን ጥቅም ባልነካ መልኩ እንደሚፈጸምና ለመጨረሻ ውሳኔ ነገ ከወኪሉ ጋር ቀጠሮ መያዙን ስራ አስኪያጁ አቶ አቢዮት ብርሃኑ ተናግረዋል።
የፋሲል ከነማ የ2013 የኢትዮዽያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረገው አጥቂው ሙጂብ ቃሲም ለአልጄሪያው ጂኤስ ካባሊ ለቀጣዮቹ 3 አመታት ለመጫወት ከስምምነት ላይ መደረሱን ደግሞ ወኪሉ ሳሚ ነስሮ ተናግሯል።
ጉዳዩን ከሚያውቁት ውስጥ አዋቂዎች የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው ክለቡ 100 ሺ ዶላር ጠይቆ የነበረ ሲሆን እድሉ ለክለቡም ሆነ ለሀገር ትልቅ ጥቅም ይኖረዋል በሚል ወደ 30ሺህ ዶላር ዝቅ መጠየቃቸውመውረዱ ታውቋል።
የአልጄሪያው ክለብ በአፍሪካ መድረክ ጥሩ ውጤት አላቸው ከሚባሉ ክለቦች መሃል ሲሆን ሁለት የሻምፒየንስ ሊግ፣ አንድ የኮንፌዴሬሽን ካፕ፣ ሶስት የአሸናፊዎች አሸናፊ አንዲሁም 14 ጊዜ የአልጄሪያ ሊግን በድል የፈጸመ ክለብ ነው። ክለቡ የአልጄሪያን ፕሮፌሽናል ሊግን 14 ጊዜ ያሸነፈበት የሀገሪቱ ሪከርድ ሆኖ ተመዝግቧል።
በጉዳዩ ዙሪያ የአልጄሪያው ጂ ኤስ ካባሊ ለፋሲል ከነማ ይፋዊ ጥያቄ ባያቀርብም በጉዳዩ ላይ ሁለቱንም ወገኖች የሚያስማማ ስምምነት ላይ ለመድረስ ክለቡና የሙጂብ ወኪል ሳምሶን ነስሮ ነገ ለመጨረሻ። ውሳኔ ቀጠሮ መያዛቸው ታውቋል።
ኦኪኪ አፎላቢን ያስፈረሙት ፋሲል ከነማዎች በዚሁ አጥቂ ይቀጥሉ ወይም ተጨማሪ አጥቂ ያስፈርሙ ከቀናት በኋላ የሚታወቅ ይሆናል።
አስተያየት ይስጡ