ደቡብ አፍሪካዊዉ የቀድሞ የፈረሰኞቹ አሰልጣኝ ማሂር ዳቪድስ የቀድሞ ክለቡን ቅዱስ ጊዮርጊስ ለፊፋ ሊከስ እንደሆ የአሰልጣኙ ወኪል ራስተም ሳይመንስ ገልጿል።
ከጥቅም 2012 ዓ.ም አንስቶ ክለቡን ማሰልጠን የጀመረው አሰልጣኝ ማሂር ከስድስት ወራት ቆይታ በኋላ ከአራት ወር በፊት በወርሀ መጋቢት ከክለቡ መሰናበቱ ይታወሳል።
ከክለቡ ከተሰናበተ በኋላ ወደ ሀገሩ በማምራት አሁን ላይ ማሪዝበርግ ዩናይትድ የተባለውን ክለብ በምክትል አሰልጣኝነት በማሰልጠን ላይ የሚገኙዉ ማሂር ዳቪድስ የቀድሞ ክለቡ ቅዱስ ጊየርጊስ እስከ አሁን ድረስ የሁለት ወር ከግማሽ ክፍያ እንዳልፈፀመለት ተናግሯል። በተደጋጋሚ የክለቡ ሰዎች ቃል ቢገቡለትም ቃላቸዉን ጠብቀው ክፍያዉን ሊፈፅሙ ባለመቻላቸው ምክንያት እና ጉዳዩን በተመለከተ ለኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ደብዳቤ ብንልክም ይፋዊ የሆነ ምላሽ ከፌዴሬሽኑ ሊሰጠን ባለመቻሉ ጉዳዩን ወደ ፊፉ በመዉሰድ ክስ ሊመሰርቱ መሆናቸውን ወኪሉ ራስተም ሳይመንስ ለሀትሪክ ስፖርት ገልጿል ። በጉዳዩ ዙሪያ የቅዱስ ጊዮርጊስ አመራሮችን ለመጠየቅ ያደረገነው ጥረት ለግዜው አልተሳካም።
አስተያየት ይስጡ